Daily Weather Report 25 June 9

Weather Summary for previous day

June 8, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ነጆ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ ደምብዶሎ፣ ጊዳአያና፣ ጨዋቃ፣ ሻምቡ፣ አርጆ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ካቺሴ፣ ጎንደር፣ ቻግኒ፣ ኢጃጂ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ ሆሳዕና፣ ሐዋሳ፣ ቦሬ፣ ዲላ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ እና ጅግጅጋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንገርጉትን፣ በጊምቢ እና በጋቲራ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በፉኝዶ፣ ጨፋ፣ ዳሊፋጊ፣ ሸዋሮቢት፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ አይሻ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ከ36.0-41.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over our country's western, northwestern, southwestern, southern, central, and eastern regions. In this regard, Nedjo, Gimbi, Aira, Dembidolo, Gidayana, Chewaka, Shambu, Arjo, Gambella, Fugnido, Gore, Gatira, Jimma, Chira, Kachise, Gondar, Chagni, Ijaji, Ambo, Weliso, Addis Ababa, Hosaina, Hawassa, Bore, Dilla, Balerobe, Haromaya, and Jigjiga received light to moderate rainfall. Moreover, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Angergutin, Gimbi, and Gatira. In contrast, the maximum temperature of the day was recorded in Fugnido, Cheffa, Dalifagi, Shewarobit, Awash Arba, Metehara, Aisha, Dire Dawa, Gode, and Kebridehar, ranging from 36.0 to 41.5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 10, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መኖር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ዳዋ፣ ሊበን እና ቆራሄ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ካማሽ፣ መተከል፣ አሶሳ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ኤሊዳር፣ አሳይታ፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ መተማ፣ ቋራ እና መተከል ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the upcoming day, weather conditions conducive to rain will be more intense, particularly in the country's western and north-western parts. In this respect, from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west and southwest Shewa, Guji and west Guji, Bale, west Arsi and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from Benishangul Gumuz region Asossa, Kamashi, Metekel and Mao Komo zones; from Amhara region west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from Tigray region west and north west zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro from South west Ethiopia region; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Kore and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Fafen, Jarar, Dawa, Liben and Korahe zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, west and central Gondar, Awi zone, Kamashi, Metekel, Asossa, west and east Wellega zones will experience heavy rain of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, numerical forecast indicates that the maximum daily temperature will be recorded above 38 degrees Celsius in Samara, Chifra, Dubti, Elidar, Asaita, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, Metema, Quara, and Metekal.