Daily Weather Report 25 June 8

Weather Summary for previous day

June 7, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፣ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ደሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ጋርዱላ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ቡኖ በደሌ፣ጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ቋራ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ዱብቲ፣ዳሊፋጌ፣ ገዋኔ፣ ጭፍራ፣ መተከል፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be cloudy weather over the western, northwestern, central, eastern, and southern regions of our country. Additionally, the western and northwestern zones of the Tigray region; the western, northern, central, and southern parts of Gondar in the Amhara region; Awi zone; western and eastern zones of Gojjam; the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, Horo Guduru, western and eastern Wollega; western, southwestern, northern, and eastern Shewa; Guji and western Guji; Borena and eastern Borena; Bale and eastern Harerge zones in Oromia; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, western Omo, and Dawuro zones in the South West Ethiopia region; Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Gardula, and Gedeo zones in the Southern Ethiopia region; Sidama region zones; Gurage, eastern Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kambaata, and Tambaro zones in the Central Ethiopia region; Agnuak, Majang, and Itang zones in Gambela; Metekel, Asosa, Kamashi, and Mao Komo zones in Benishangul-Gumuz; and the Fafen zone in the Somali region are expected to receive rainfall ranging from light to moderate intensity (1-29 mm).Moreover, in the Kellem, western and eastern Wollega, Buno Bedele, Jimma, and Ilubabor zones, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is anticipated. On the other hand, in Humera, Metema, Metehara, Quara, Gambela, Lare, Abobo, Funyido, Dire Dawa, Semera, Dubti, Dallifage, Gewane, Chifra, Metekel, Elidar, Awash Arba, Aisha, and Gode, daytime temperatures are expected to reach highs above 38 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 9, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሸካ ዞን፤ በጌዲኦ ዞን ፤ በሲዳማ፤ በአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማሻ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡በሌላ በኩል በመተሐራ፣መኢሶ፣ድሬዳዋ፣ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0 እስከ 38.6 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were cloudy conditions in the western, southern, and southwestern regions of our country. Additionally, in Sheka Zone, Gedeo Zone, Sidama, and the zones of Agnuak, Majang, and Itang, as well as in Jimma, Buno Bedelle, Horo Guduru, and Kellem Wollega zones, light to moderate rainfall was recorded. Furthermore, in Masha, heavy rainfall exceeding 30 millimeters was reported. On the other hand, in Metehara, Meiso, Dire Dawa, Funyido, and Gode, the daytime temperatures reached a high range between 36.0 and 38.6 degrees Celsius.