Daily Weather Report 25 June 7
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ፤ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤በጉራጌ ዞን፤ በጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ፤ ኢታንግ ዞን ፤ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ምዕራብ ጉጂ፣ባሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ ና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች እንዲሁም አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡በሌላ በኩል በመተሐራ፣ድሬዳዋ፣ፉኝዶ፣ ጎዴ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0 እስከ 38.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloudy haze over the western, central, southern, and southwestern parts of our country. Additionally, in the western zones of Gondar, Awi, western and eastern Gojjam; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Dawuro, and western Omo zones; Gurage zone; Gamo and southern Omo zones; Itang zone; western, southwestern, and northern Shewa; western Guji, Bale, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, and eastern Wollega zones; as well as in Addis Ababa, light to moderate rainfall was recorded. Furthermore, in Nekemte, heavy rainfall exceeding 30 mm was observed. On the other hand, in Metehara, Dire Dawa, Fugnido, Gode, and Gambela, daytime maximum temperatures ranged from 36.0 to 38.2 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፣ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ደሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ዳዋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ቋራ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ዱብቲ፣ዳሊፋጌ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for rainfall will continue across western, northwestern, central, eastern, and southern parts of our country under similar patterns. Accordingly, rainfall ranging from light to moderate intensity (1-29 mm) is expected in the western and northwestern zones of Tigray region; western, northern, central, and southern parts of Amhara region including Gondar, Awi zone, and western and eastern zones of Gojjam; the zones of Jimma, Ilu Aba Bora, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, western and eastern Wollega, western, southwestern, northern, and eastern Shewa, Guji and western Guji, Borena and eastern Borena, Bale, Arsi and western Arsi, eastern and western Harerge zones of Oromia region; Addis Ababa, Harar, and Dire Dawa; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, western and Dawuro zones of South West Ethiopia region; Wolayita, Gofa, Gamo, Basketo, Gardula, Kore, South Omo, and Gedeo zones of Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region (SNNPR); Gurage, Silte, Hadiya, Halaba special zone, and the special zones of Yem, Kambata, and Tambaro in Central Ethiopia; Agnuak, Nuer, Majang, and Itang zones of Gambela region; Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; and Fafan and Dawa zones of Somali region will receive rainfall. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is anticipated in Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, western and eastern Wollega, Jimma, and Ilu Aba Bora zones.Moreover, maximum daytime temperatures exceeding 38 degrees Celsius are expected in Humera, Metema, Metehara, Quara, Gambela, Lare, Abobo, Funyido, Dire Dawa, Semera, Dubti, Dallifage, Gewane, Elidar, Awash Arba, Aisha, and Gode areas, according to meteorological forecasts.