Daily Weather Report 25 June 5

Weather Summary for previous day

June 4, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዞም በጎንደር፣ ሻዉራ፣ ደብረ ታቦር፣ ሞጣ፣ ዳንግላ፣ ላይ በር፣ አሶሳ፣ ሸርኮሌ፣ ጊዳ አያና፣ ጊምብ፣ ነቀምቴ፣ አይራ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ቡሬ፣ ጅማ፣ ሊሙ ገኔት፣ ነገሌ፣ እጃጂ፣ ቴፒ፣ ሀዋሳ፣ ምዕራብ አባያ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሀረር እና ሐሮማያ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአዋሽ አርባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ጎዴ፣ ገዋኔ፣ መተሀራ እና ሰመራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage in the western, eastern, central, southwestern and southern regions of our country. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Gondar, Shaura, Debre Tabor, Motta, Dangila, Lay Ber, Asossa, Sherkole, Gida Ayana, Gimbi, Nekemte, Aira, Bedele, Gore, Chira, Bure, Jimma, Limmu Genet, Negele, Ejaji, Tepi, Hawassa, West Abaya, Dire Dawa, Harar and Haromaya. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Awash Arba, Dire Dawa, Gode, Gewane, Metehara and Semera.

Weather Forecast for next day

June 6, 2025

በነገዉ ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ፣ መካከለኛ እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ጥንካሬ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ፣ ከምባታ እና ጠንባሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋሞ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር፣ ኢታንግ፣ ማጃንግና አኙዋክ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ መተከል፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ከፋ እና ሸካ ዞኖች በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በዱብቲ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ቋራ እና ሁመራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow rain-producing weather events will continue with the same intensity in the North, West, Southwest, South, Central, and East parts of our country. In line with this , from the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo, Dawro, Kembata and Tanbaro zones; from the Central Ethiopian Region, Gurage, Hadiya, Halaba, Silte, Yem Zone; from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gofa, Basketo, Gamo and Gedeo zones; from the Gambella Region, Nuer, Itang, Majang and Agniwak zones; from the Oromia Region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South-West Shewa, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; From Tigray region Central, Northwestern and Western zones; Addis Ababa; Dire Dawa, Harar; Sidama region zones; From Central, North, West and South Gondar, Awi zone, West and East Gojam zones of Amhara region; and Asossa, Metekel, Kemash and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, South Gondar, Awi Zone, Metekel, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, Kefa and Sheka Zones will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 38 degrees Celsius in Dubti, Semera, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Metema, Quara and Humera.