Daily Weather Report 25 June 4

Weather Summary for previous day

June 3, 2025

በትናንትናው ዕለት በላይበር፣ ጊምቢ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ጨዋቃ፣ ቡሬ፣ ጋምቤላ፣ ሶኮሩ፣ ማሻ፣ ሳዉላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ ደሎመና፣ ጃራ እና አደሌ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ዳሊፋጊ፣ ገዋኔ፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ መተማ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ከ36-43 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Laiber, Gimbi, Shambu, Nekemte, Arjo, Chewaka, Bure, Gambella, Sokoru, Masha, Sawula, Walaita Sodo, Dilla, Bore, Delomanna, Jara, and Adele had cloud coverage and received light to moderate rain. In contrast, in Semera, Chifra, Dalifagi, Gewane, Aisha, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Metema, Gode, and Kebridehar, the maximum temperature of the day was recorded at 36-43 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 5, 2025

በነገው ዕለት ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭትም የተለያዩ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ካማሽ፣ መተከል፣ አዊ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ አሳይታ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጊ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow’s forecast shows that the moist weather entering our country will continue to strengthen in the country's west, southwest, northwest, and central parts. In this regard, from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, Southwest and east Shewa, Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from Benishangul Gumuz region Asossa, Kamashi, Metekel and Mao Komo zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Majang and Itang; from the central Ethiopian region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region, west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from Tigray region west and north west zones; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Kore and Gedeo zones and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). The amount and distribution of this rain will be crucial for conducting various agricultural activities. In addition, Kamashi, Metekel, Awi, east Wellega, and Jimma zones will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature will be recorded exceeding 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Asaita, Chifra, Semera, Dubti, Mile, Awash Arba, Gewane, Aisha, Dalifagi, and Metehara.