Daily Weather Report 25 June 30

Weather Summary for previous day

June 29, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ነፋስመዉጫ፣ ላሊበላ፣ መካነሰላም፣ ወራኢሉ፣ መሀልመዳ፣ እነዋሪ፣ ሾላገበያ፣ ቡለን፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ አንገርጉትን፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ኢጃጂ፣ ካቺሴ፣ ጉንዶመስቀል፣ አዲስ አበባ፣ አቦምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ቦሬ፣ ተርጫ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ ዲላ እና ቁሉቢ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመልካጀበዱ፣ አይሻ፣ መተሀራ፣ ቀብሪዳሃር እና ድሬዳዋ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.8 እስከ 40.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over parts of the country that benefited from the Kiremt rain. In this regard, light to moderate rains were experienced in Debark, Gondar, Ayikel, Shahura, Bahirdar, Dangila, Adet, Motta, Nefasmewcha, Lalibela, Mekaneselam, Wareilu, Mehalmeda, Enewari, Sholagebeya, Bulen, Nedjo, Gimbi, Aira, Angergutin, Arjo, Nekemte, Shambu, Bedele, Gore, Gatira, Chira, Jimma, Sokoru, Ijaji, Kachise, Gundomeskel, Addis Ababa, Abomsa, Arsirobe, Bore, Tercha, Arba Minch, Jinka, Dilla and Kulubi. On the other hand, the maximum daily temperatures in Melkajebedu, Aisha, Metehara, Kebridahar and Dire Dawa were recorded at 37.8 to 40.5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

July 1, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ፣ ማሂ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቀለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሊቦከምከም፣ ደምቢያ፣ ፎገራ፣ እስቴ፣ ጎንደር ዙሪያ፣ ሁለትእጅነሴ፣ ሸበልበርንታ፣ ደላንታ፣ ማኦኮሞ፣ ቤጊ፣ ጊዳሚ፣ አንፍሎ፣ ነጆ፣ ጉሊሶ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ ኖሌካባ፣ ደራ፣ ላሬ፣ አኮቦ፣ ጆሬ፣ እና ጋምቤላ ዙሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና መተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the upcoming day, the forecast indicates that weather conditions favorable to the occurrence of Kiremt rain will continue to strengthen in the western half, central, northeastern, and eastern parts of the country. In this respect, the west, north west, central, south, south east and east zones of Tigray region; the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo national special zone, Waghemra and north Shewa zones of Amhara region; Metekal, Asossa, Mao Komo and Kamash zones Benishangul Gumuz region; Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi, Mahi and Hari zones of Afar region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and west Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones of Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Majang, Nuwer, Itang and Agnuak zones Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones the south west Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones of the central Ethiopia region; Walaita, Basketo, Gofa and Gedeo zones of the south Ethiopia region; Sidama region zones and Somali region’s Siti and Fafen zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Libokemkem, Dembiya, Fogera, Este, Gondar Zuria, Hullet Ejnesse, Shebelbernta, Delanta, Mao Komo, Begi, Gidami, Anfilo, Nedjo, Guliso, Gimbi, Aira, Nolekaba, Dera, Lare, Akobo, Jore, and Gambella Zuria will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Semera, Chifra, Dubti, Mile, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, and Metema.