Daily Weather Report 25 June 3
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እና አማራ ክልል ደቡባዊ ክፍል የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ቡሌሆራ፣ ያቤሎ፣ ጋምቤላ፣ አማን፣ ማሻ፣ ማጂ፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ቡርጂ፣ ላይበር እና ደብረማርቆስ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37-43.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over western, central, and southern Oromia; Gambella; southwestern and southern Ethiopia, and the southern part of Amhara region. Consequently, Gidayana, Nekemte, Bedele, Gore, Bure, Chira, Jimma, Ambo, Bulehora, Yabelo, Gambella, Aman, Masha, Maji, Tepi, Tercha, Sawula, Jinka, Burji, Laiber, and Debremarkos received light to moderate rainfall. On the other hand, in Chifra, Semera, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, and Aisha, the day's maximum temperature was recorded at 37-43.4 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭትም የተለያዩ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ሸካ፣ ከፋ፣ ኢሉባቦር እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጊ፣ መተማ እና መተከል ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the upcoming day, the southwestern, western, northwestern, central, and eastern areas of the country will have better cloud coverage. In this regard, from the southwest Ethiopian region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa, west Guji, Borena, Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the central Ethiopian region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Majang and Itang zones; from Benishangul Gumuz region Asossa, Kamashi, Metekel and Mao Komo zones; from Amhara region west, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; Sidama region zones and the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardula and Gedeo zones of south Ethiopia region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). The amount and distribution of this rain will be crucial for conducting various agricultural activities. Moreover, Sheka, Kefa, Ilubabor, and Jimma zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast information indicates that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Samara, Elidar, Dubti, Mile, Awash Arba, Gewane, Aisha, Dalifagi, Metema, and Metekal.