Daily Weather Report 25 June 28

Weather Summary for previous day

June 27, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይከል፣ ሻሁራ፣ ደ/ታቦር፣ሞጣ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ቡለን፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ በዴሌ፣ ጂማ፣ ጪራ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ አይራ፣ የትኖራ፣ ጎሬ፣ አሶሳ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ጂንካ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ እምድ ብር እና መቐሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በካቺስ እና ቢላቴ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሀራ፣ መኢሶ፣ ዳሮር፣ ድሬዳዋ፤ ባቲ, ኑርኢራ እና መልካ ጀብዱ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2 እስከ 41.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were cloudy conditions in the northern, northwestern, central, and western regions of our country. Additionally, areas such as Aykel, Shahura, Debre Tabor, Motta, Chagni, Dangila, Bullen, Bahir Dar, Debre Markos, Nekemte, Arjo, Bedele, Jimma, Chira, Woliso, Addis Ababa, Ayira, Yitinora, Gore, Asosa, Tepi, Aman, Jinka, Wolayita Sodo, Arba Minch, Emdibir, and Mekelle experienced rainfall ranging from light to moderate intensity. In Kachis and Bilate, heavy rainfall exceeding 30 millimeters was recorded. On the other hand, in Metahara, Meiso, Daror, Dire Dawa, Bati, Nura era, and Melka Jebdu, daytime temperatures were notably high, ranging from 35.2 to 41.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 29, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ምዕራብ ጉጂ ፣ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ አኮቦ፣ ጆሬ፣ ጎግ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ ዙሪያ፣ ጊዳሚ፣ አንፍሎ፣ ሰዮ፣ ቡሬ፣ ጌራ፣ ደቢ ዶሎ፣ ቤጊ፣ ጉባ ፣ አለፋ፣ ጃዊ፣ ቋራ እና ቡለን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በኤሊዳር፣መተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መልካ ጀብዱ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ እና አይሻ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆኑ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, areas of our country that benefit from winter rain will experience thick and widespread cloud cover. Along with this, regions including the western, northwestern, central, eastern, southern, and southeastern zones of Tigray; the western, northern, central, and southern parts of Amhara such as Gondar, Awi Zone, western and eastern Gojjam, northern and southern Wollo, Wag Himra; Oromo Ethnic special zones and northern Shewa; Metekel, Asosa, Kamashi, and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz; Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, Horo Guduru, western and eastern Wollega, northern, eastern, western, and southern Western Shewa; Arsi and western Arsi, western and eastern Hararge, western Guji, Bale; Addis Ababa and Dire Dawa; Agnuak, Majang, and Itang zones in Gambela; Bench Sheko, Sheka, Kaffa, Konta, western Oromo, and Dawuro in southwestern Ethiopia; Gurage, eastern Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kambata, and Tambaro in central Ethiopia; Wolayita, Gofa, Gamo, and Gedeo in southern Ethiopia; zones of Sidama and the Sitti zone of Somali region will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 millimeters in many locations. Additionally, areas such as Mao-Komo, Akobo, Jore, Gog, Abobo, around Gambela, Gidami, Anfilo, Sayo, Bure, Gera, Debi Dolo, Begi, Guba, Alefa, Jawi, Quara, and Bullen are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 millimeters within 24 hours. On the other hand, in places like Elidar, Metema, Gambela, Funyido, Melka Jebdu, Chefa, Bati, Metehara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Chifra, Dubti, Semera, and Aisha, daytime temperatures are to rise above 38 degrees Celsius, according to our meteorological predictions.