Daily Weather Report 25 June 27

Weather Summary for previous day

June 26, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመተማ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ሸንዲ፣ እሮብገበያ፣መካነኢየሱስ፣ኮሶ ባር፣አዲስ ዘመን፣ደ/ታቦር፣ሞጣ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ካቺስ፣ ወሊሶ፣ሻምቦ፣ጂማ፣ጪራ፣ጎሬ፣ደቢ ዶሎ እና ታርጫ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡለን፣ጊምቢ፣ኢጃጂ እና በበደሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሀራ፣ ጨፋ፣ መተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣መኢሶ እና መልካ ጀብዱ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4 እስከ 41.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloudy atmosphere in the northern, central, and western regions of our country. Along with this, moderate to light rainfall was recorded in Metema, Aykel, Shahura, Shendi, Robgeba, Mekane Jesus, Koso Bar, Addis Zemen, Debre Tabor, Motta, Chagni, Dangila, Kachis, Woliso, Shambu, Jimma, Chira, Gore, Dembidolo, and Tercha. Heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Bullen, Gimbi, Ejaji, and Bedelle. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.4 to 41.0 degrees Celsius were recorded in Metahara, Cheffa, Metema, Gambela, Funyido, Meiso, and Melka Jebdu.

Weather Forecast for next day

June 28, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ሲቲ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ አኮቦ፣ ጆሬ፣ ጎግ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ ዙሪያ፣ መንገሽ፣ ጊዳሚ፣ አንፍሎ፣ ሰዮ፣ ቡሬ፣ ሰተማ፣ ጌራ፣ ማሻ እና ጌሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በኤሊዳር፣መተማ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ አይሻ እና ቀብሪደሃር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆኑ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloudy weather accompanied by beneficial winter rain over various regions of our country. Specifically, the central, eastern, southern, and southeastern zones of the Tigray region; the western, northern, central, and southern parts of the Amhara region including Gondar; the Awi zone; the western and eastern parts of Gojjam; the northern and southern parts of Wollo; Wag Himra; Oromia Ethnic special zone; and northern Shewa. In the Benishangul Gumuz region, areas such as Metekel, Asosa, Kamashi, and Mao-Komo will also experience rain. In Oromia, rainfall is expected in Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horro Guduru, the western and eastern parts of Wollega, northern, eastern, western, and southern western Shewa, Arsi and western Arsi, Borena, western and eastern Hararghe, Bale, Addis Ababa, Harar, and Dire Dawa. From the Gambela region, the Agnuak, Majang, and Itang zones will receive rain. In the Southern Western places like Bench Sheko, Sheka, Kaffa, Konta, western Omo, and Dawuro; in the Central Ethiopia region, Gurage, eastern Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, the Yem special zone, Kambata, and Tambaro; and in the Southern Ethiopia region, Wolayita, Gofa, Gamo, and Gedeo zones, as well as the zones of Fafan and Sitti in the Somali region, will experience light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 millimeters in many of their locations. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 millimeters within 24 hours is expected in areas such as Mao-Komo, Akobo, Jore, Gog, and Abobo, around Gambela, Mangesh, Gidami, Anfilo, Sayo, Bure, Setema, Gera, Masha, and Gash. On the other hand, forecasts indicate that daytime temperatures in Elidar, Metema, Chefa, Bati, Metehara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Chifra, Dubti, Semera, Ayshe, and Kebridahar will rise above 38 degrees Celsius.