Daily Weather Report 25 June 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመተማ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህር ዳር፣ አባይሸለቆ፣ አሸር፣ ሸንዲ፣ እሮብገበያ፣ ቡሬ፣ መካነኢየሱስ፣ መርጦለማርያም፣ ደብረወርቅ፣ ቻግኒ፣ ላይበር፣ ደ/ታቦር፣ ላሊበላ፣ ፓዌ፣ አምቦ፣ ካቺስ፣ ወሊሶ፣ ቦሬ፣ ሆሮዶየ፣ ገለምሶ፣ አዲስ አበባ እና አቃቂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በዳንግላ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ቀብሪደሀር፣ ኑራኤራ፣ ማጀቴ፣ መተማ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud coverage over the northwest, central, west, and east parts of our country. In this regard, Metema, Aykel, Shahura, Bahir Dar, Abayshelleko, Asher, Shendi, Erobgebeya, Bure, MekaneEeysus, Mertolemariam, Debrework, Chagni, Leiber, DebreTabor, Lalibela, Pawe, Ambo, Kachis, Woliso, Bore, Horodoye, Gelmso, Addis Ababa, and Akaki received light to moderate rainfall, additionally more than 30 heavy rainfalls were recorded in Dangla within 24 hours. On the other hand, in Aisha, Dire Dawa, Metehara, Cheffa, Bati, Kebridehar, Nuraera, Majete, Metema, and Gode, the highest temperature of the day recorded exceed 35.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በለጋምቦ፣ ኩዩ፣ ግንደበረት፣ ሜታዋልቂጤ፣ ድቅሲስ፣ ሱዴ፣ ነንሴቦ፣ ዶዶላ፣ አዳባ እና ገና 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ አይሻ እና ቀብሪደሃር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆኑ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the Kiremt rainfall benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region northwest, central, eastern, southern and southeastern zones; from Amhara region western, northern, central, and southern Gondar, Awi zone; western and eastern Gojjam; northern and southern Wollo; Waghemra, Oromo Ethnic Special zone and northern Shewa Zones; from the Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamash, and Maokomo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Kelem, Horo Guduru, western and eastern Wellega, northern, eastern, western, and southwestern Shewa, Arsi and western Arsi, western and eastern Hararge, Bale, Guji and western Guji zones; Addis Ababa; Harari; from Gambella region: Angwuak, Majang, and Itang zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dauro zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Southern Ethiopia region the Wolayta, Gofa, Gamo, and Gedeo zones; Sidama regional zones; and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many areas. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected in Legambo, Kuyu, Gindeberet, Metawalkite, Diksis, Sude, Nensebo, Dodola, Adaba, and Gena within 24 hours. On the other hand, our numerical forecast indicates that maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Metema, Cheffa, Bati, Metehara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Dubti, Semera, Aisha, and Kebridehar.