Daily Weather Report 25 June 24

Weather Summary for previous day

June 23, 2025

በትናንትናው ዕለት በመተማ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ሞጣ፣ መካነሰላም፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ፓዌ፣ ቡለን፣ ጋምቤላ፣ አበብርጋ፣ ማሻ፣ ነቀምቴ፣ ደምብዶሎ፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ተርጫ፣ ጂንካ፣ ሐዋሳ እና ዲላ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በጎሬ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ መተሀራ፣ ጎዴ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሎል፣ መልካጀብዱ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Metema, Gondar, Bahir Dar, Mota, Mekane selam, Chagni, Dangla, Pawe, Bulen, Gambella, Abebrga, Masha, Nekemte, Dembdolo, Jimma, Addis Ababa, Emdbir, Hosanna, Tercha, Jinka, Hawassa and Dilla had cloud cover and received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was also recorded in Gore. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 36 degrees Celsius in Aisha, Metahara, Gode, Dire Dawa, Dallol, Melkajebdu and Metema.

Weather Forecast for next day

June 25, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቀለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል በጥቂት ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ሆሮ፣ ቡሬ፣ ሰዮ፣ መቱ፣ ያዩ፣ ማሻ፣ የኪ፣ ኢጃጂ፣ ሊቦከምከም እና አድዋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ማጃንግ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ መተማ እና ፉኝዶ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, west, central, southwest, northeast and east areas of the country. In addition, the west, northwest, central, south, southeast and east zones of Tigray region; the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojam, north and south Wollo, Oromo National Special Zone, Waghemra and North Shewa zones; from Benishangul Gumuz region, Metekal, Asosa, Maokomo and Kamash zones; from Oromia region, Yeima, Ilubabor, Buno Bedele, Rika, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West, South-West and East Shewa, Guji and West Guji, East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Majang, Nuer, Itang and Agnuak zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Wolaita, Basketo and Gedio zones from Southern Ethiopia region; Sidama region zones and In Somali region, some areas of Dawa, Liben, Afder, Shebelle and Jarar zones will experience light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, Jimma Horo, Bure, Seyo, Metu, Yau, Masha, Yeki, Ijaji, Libokemkem and Adwa will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the highest temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Samara, Chafra, Dubti, Mile, Elidar, Aisha, Gewane, Ilubabor, Sheka, Majang, Dalifagi, Awash Arba, Metahara, Metema and Fugendo.