Daily Weather Report 25 June 23

Weather Summary for previous day

June 22, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎንደር፣ አይከል፣ ደ/ ታቦር፣ ቻግኒ፣ ሸርኮሌ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ ካቺስ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ቦሬ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካ ጎርዶዬ፣ ጀልዱ፣ ቦረያ እና አቃቂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በተጨማሪም በጊዳአያና እና አንገርጉትን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሀራ፣ ጨፋ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the areas of our country that benefited from the winter rains had cloud cover. In this regard, Gondar, Aykel, De/ Tabor, Chagni, Sherkole, Nejo, Aira, Gimbi, Nekemte, Shambu, Ijaji, Kachis, Ambo, Woliso, Gore, Jimma, Bore, Emdbir, Hosanna, Dilla, Wolaita Sodo, Jinka Gordoye, Jeldu, Boraya and Akaki received light to moderate rain; In addition, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Gidayana and Angerugut within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 35.0 degrees Celsius in Metahara, Chefa, Dire Dawa, Aisha, Kebridehar and Gode.

Weather Forecast for next day

June 24, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአድዋ፣ አዲግራት፣ ሀውዜን፣ ገረአልታ፣ እዳጋ ሐሙስ፣ ጃዊ፣ ደቡብና ሰሜን አቸፈር፣ ዳንግላ፣ አዲስ ቅዳም፣ ቻግኒ፣ እንጂባራ፣ ቲሊሊ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ሆሮ ቡልቂ፣ ጉዱሩ፣ ሻምቡ፣ ሊሙ፣ አንፊሎ፣ ጊዳሜ እና ጀልዱ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ መተማ፣ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆኑ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of kiremet rains will be stronger in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the West, North West, Central, East and South East zones of Tigray Region; the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo of Amhara Region; Waghemra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; Asosa, Metekel, Kamash and Maokomo Zones from Benishangul Gumuz Region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, East, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararge Arsi and West Arsi Zones from Oromia Region; Addis Ababa; The Anuak zone of Gambella region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of Southwestern Ethiopia region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedio zones of Southern Ethiopia region and the Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Additionally, Adwa, Adigrat, Hawzen, Geralta, Edaga Khamus, Jawi, South and North Achefer, Dangla, Addis Qadam, Chagni, Innibara, Tillili, Fnote Selam, Horo Bulki, Guduru, Shambu, Limu, Anfilo, Gidame and Jeldu will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, our numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will be above 38 degrees Celsius in Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Semera, and Metama.