Daily Weather Report 25 June 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደ/ ታቦር፣ ላሊበላ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ደ/ማርቆስ፣ መካነ ሰላም፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ካቺስ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ባቱ፣ ቦሬ፣ አዲስ አበባ፣ ሰኮሩ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳውላ፣ ብላቴ፣ አርባምንጭ፣ ኮንሶ፣ ማጂ፣ አማን፣ አጋሮ፣ ባቢሎ፣ ፈገልታ እና ኦሞንታ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ጨፋ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northeast, northwest, central, western and southern regions of our country had cloud cover. In connection with this, there were also clouds in De/ Tabor, Lalibela, Bahir Dar, Chagni, Dangla, De/ Markos, Mekane Selam, Nekemte, Bedele, Gatira, Jimma, Ambo, Kachis, Ambo, Woliso, Bishoftu, Bui, Batu, Bore, Addis Ababa, Sekoru, Emdbir, Hosanna, Warabe, Tercha, Wolaita, Sodo, Saula, Bilate, Arbaminch, Konso, Maji, Aman, Agaro, Babilo, Fegelta and Omonta received light to moderate rainfall. On the other hand, Fugendo, Metahara, Chefa, Dire Dawa and Gode recorded the highest temperature of the day above 35.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የተስፋፋና ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአዲግራት፣ ሀውዜን፣ ገረአልታ፣ እዳጋ ሐሙስ፣ ውቅሮ፣ ምዕራብና ምስራቅ ደምቢያ፣ ምዕራብና ምስራቅ በለሳ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ማኦኮሞ፣ ኢፋታ፣ አምቦ ዙርያ፣ ዳዋ፣ አመያ፣ አዲስ አለም፣ ወሊሶ፣ ጎሮ፣ ጨና፣ ጀሙ፣ ዴቻ፣እና ጊምቦ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ መተማ፣ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆኑ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be widespread and strong cloud cover and accumulation in the northwest, northeast, west, central and south regions of our country that benefit from kiremet rains. In connection with this, the west, northwest, central, east and southeast zones of Tigray region; the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojam, north and south Wollo, Waghmare, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; Asosa, Metekel, Kamash and Maokomo Zones from Benishangul Gumuz Region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararge and West Arsi Zones from Oromia Region; Addis Ababa; Anuak Zone from Gambella Region; The Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region and the Sidama Region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Additionally, Adigrat, Hawzen, Geralta, Edaga, Khamus, Hugro, West and East Dembia, West and East Belsa, Amba Giorgis, Maokomo, Ifata, Ambo Zuria, Dawa, Amea, Addis Alem, Wolisso, Goro, Chena, Jemu, Decha, and Gimbo will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, our numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will be above 38 degrees Celsius in Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Semera, and Metama.