Daily Weather Report 25 June 21

Weather Summary for previous day

June 20, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ደ/ ታቦር፣ ላሊበላ፣ አዴት፣ ዳንግላ፣ የትኖራ፣ መካነሰላም፣ ጉንደመስቀል፣ አሶሳ፣ ቡለን፣ ደምቢዶሎ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ነቀምቴ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ወሊሶ፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ ሚኤሶ፣ ዶሎመና፣ ያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ ቡኢ፣ አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ ባምቢስ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ማጂ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ብላቴ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ሀዋሳ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በተጨማሪም በበደሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ጨፋ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the Kiremt benefiting area over the northern, northwestern, central, western, and southern parts of our country. In association with this, light to moderate rainfall was recorded in Mekelle, Debarq, Gondar, Aykel, Shahura, Debre Tabor, Lalibela, Adet, Dangla, Yetnora, Mekaneselam, Gundomeskel, Asosa, Bulen, Dembidolo, Aira, Gore, Nekemte, Limugenet, Jimma, Wolisso, Shambu, Kachis, Mieso, Dolomena, Yabelo, Bulehora, Bui, Addis Ababa, Gambella, Asosa, Bambis, Tepi, Aman, Maji, Hosanna, Warabe, Bilate, Wolayta, Sodo, Burji, Konso, and Hawassa; in addition, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Bedele within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 35 degrees Celsius in Fugendo, Metahara, Chefa, Dire Dawa, and Gode.

Weather Forecast for next day

June 22, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የክረምት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በጠገዴ፣ ላይ አርማጭሆ፣ ምስራቅ ደምቢያ፣ ጃዊ፣ ዳንግላ፣ አዲስ ቅዳም፣ ቻግኒ፣ እንጂባራ፣ ቲሊሊ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደምበጫ፣ ወሊሶ፣ ወንጪ፣ ጎሮ፣ አመያ፣ ሰኮሩ፣ ሊሙ ሰቃ እና ቀርሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ዳልፋጊ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ፣ መተማ፣ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation of favorable conditions for Kiremt rainfall. In line with this, the West, North West, Central, East and South East zones of Tigray Region; the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo, Wagihimara, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones of Amhara Region; the Gabi and Hari zones of Afar Region; the Assosa and Maokomo zones of Benishangul Gumuz Region; The Oromia Region’s Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East wollega, North, West and Southwest Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West and East Hararge and West Arsi zones; Addis Ababa; the Gambella Region’s Agnuak Zone; the Southwestern Ethiopia Region’s Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; the Central Ethiopia Region’s Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; the South Ethiopian Region’s Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedio zones and the Sidama Region’s zones will recieve light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Kiremt agricultural activities. In addition, Tagede, Layi Armacho, East Dembia, Jawi, Dangla, Addis Qedam, Chagni, Injibara, Tilili, Fenota Selam, Dembecha, Woliso, Wenchi, Goro, Amaya, Sekoru, Limu Seka, and Kersa will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, in Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Dalfagi, Nuraira, Semera, and Metema, the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius.