Daily Weather Report 25 June 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ላሊበላ፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ነፋስ መውጫ፣ ሞጣ፣ አዴት፣ ቻግኒ፣ ዳልፋጊ፣ ደ/ ማርቆስ፣ መሀል ሜዳ፣ እንዋሪ፣ ጉንዶ መስቀል፣ የትኖራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ዶሎመና፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ነጆ፣ ጋቲራ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ሊሙገነት፣ አርጆ፣ ኢጃጂ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ አዳማ፣ ኑራኢራ፣ አቦምሳ፣ ገለምሶ፣ አርሲ ሮቤ፣ ኩሉምሳ፣ ቡኢ፣ ሒርና፣ ቁልቢ፣ ሀረር፣ ሀሮማያ፣ ጅግጅጋ፣ አዲስ አበባ፣ ማሻ፣ ቴፒ፣ አማን፣ እምድብር፣ ሰኮሩ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ዲላ እና ሀዋሳ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በተጨማሪም በቦሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ዳልፋጊ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ፣ መተማ፣ ገዋኔ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 እስከ 45.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was widespread cloud cover in the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In this regard, Mekelle, Lalibela, Shahura, Bahir Dar, Neifs Ntul, Mota, Adet, Chagni, Dalfagi, De/ Markos, Mehal Meda, Enwari, Gundo Meskel, Tnora, Asosa, Gambella, Fugendo, Dolomena, Aira, Gore, Nejo, Gatira, Jimma, Dele, Limugenet, Arjo, Ijaji, Gidaayana, Shambu, Kachis, Wolisso, Fiche, Adama, Nuraira, Abomsa, Gelemso, Arsi Robe, Kulumsa, Bui, Hirna, Qulbi, Harar, Haromaya, Jigjiga, Addis Ababa, Masha, Tepe, Aman, Emdbir, Sekoru, Hosanna, Warabe, Dilla and Hawassa received light to moderate rainfall in many places; in addition, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Bore within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Dalfagi, Nuraira, Semera, Metama, Gewane and Aisha were recorded as 35.0 to 45.8 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የክረምት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ እና ሸካ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation in the northwest, northeast, west, central and south areas of our country that benefit from kiremet rains. In connection with this, the eastern, southern and southeastern zones of Tigray region; North, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojam, north and south Wollo, Waghkhemra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; Gabi, Fanti and Hari Zones from Afar Region; Assosa and Maokomo Zones from Benishangul Gumuz Region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West and East Hararge and West Arsi Zones from Oromia Region; Addis Ababa; The Anuak zone of Gambella region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of Southwestern Ethiopia region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedio zones of Southern Ethiopia region and the Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out winter agricultural activities. In addition, our numerical forecast data indicates that some areas of South Gondar, West Gojam, South West and West Shewa and Sheka zones will have heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperature in Samara, Elidar, Gwane, Dalifagi and Metahara is recorded at over 38 degrees Celsius.