Daily Weather Report 25 June 2

Weather Summary for previous day

June 1, 2025

በትናንትናው ዕለት ቡለን፣ ደብረማርቆስ፣ ደንብዶሎ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ አንገርጉትን፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ሶኮሩ፣ ካቺሴ፣ ኢጃጂ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ቦሬ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ተርጫ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብ አባያ እና አማን የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በዳሊፋጊ፣ ፉኚዶ፣ ሸዋሮቢት፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ከ36-42 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Bulen, Debre Markos, Denbidollo, Nedjo, Aira, Gimbi, Gidayana, Nekemte, Shambu, Angergutin, Arjo, Gore, Gatira, Jimma, Chira, Sokoru, Kachise, Ijaji, Ambo, Waliso, Addis Ababa, Bui, Emdibir, Hosaina, Bore, Hawassa, Dilla, Tercha, Arba Minch, Mirab Abaya, and Aman experienced cloud coverage and received light to moderate rain. In contrast, the maximum temperature of the day recorded in Dalifagi, Fugnido, Shewarobit, Aisha, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridehar ranged from 36 to 42 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 3, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭትም የተለያዩ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ማጃንግ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ አይሻ እና ዳሊፋጊ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the next day, cloud coverage is expected over the southwest, south, west, central, and east parts of the country. In this respect, from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardulla, south Omo and Gedeo zones; from Oromia region, Borena and east Borena, Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, west and south west Shewa zones; Addis Ababa; Harar; Sidama region zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Majang and Itang zones; from Benishangul Gumuz region Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region Awi zone and west Gojjam zones; and Somali region Dawa and Fafen zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. The amount and distribution of this rain will be crucial for conducting various agricultural activities. Besides, Majang, Sheka, Kefa, and Jimma zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Mile, Awash Arba, Gewane, Aisha, and Dalifagi.