Daily Weather Report 25 June 19

Weather Summary for previous day

June 18, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች የተጠናከረ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ አይደር፣ ሽሬእንዳስላሴ፣ ፅፅቃ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ኮምቦልቻ፣ መሀል ሜዳ፣ የትኖራ፣ ደ/ ማርቆስ፣ ሞጣ፣ ላይበር፣ ዳንግላ፣ አሶሳ፣ ቡለን፣ አዲስ አበባ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ጨዋቃ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ አምቦ፣ አዳማ፣ ኑራኢራ፣ አርሲ፣ ሮቤ፣ ቡኢ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ሻምቡ፣ ቦሬ፣ ቴፒ፣ ጂንካ፣ ሳውላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ብላቴ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ እና ሀዋሳ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በደባርቅ፣ ማንኩሽ፣ ቻግኒ፣ ጊዳአያና፣ ጊምቢ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጋምቤላ፣ ማሻ፣ አማን እና ሰኮሩ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ዳልፋጊ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ፣ ማጀቴ፣ ገዋኔ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 እስከ 45.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover in the areas of our country that benefited from the kiremt rains. In this regard, in Mekelle, Ayder, Shireendassalise, Tsitsika, Gondar, Aikel, Bahir Dar, Kombolcha, Mehal Meda, yetonora, De/ Markos, Mota, Leiber, Dangla, Asosa, Bulen, Addis Ababa, Nejo, Aira, Gore, Salutka, Arjo, Dele, Ambo, Adama, Nuraira, Arsi, Robe, Bui, Jimma,Chira, Shambu, Bore, Tepi, Jinka, Saula, Wolaita Sodo, Bilate, Hosanna, Warabe and Hawassa received light to moderate rainfall in many areas. In addition, Debark, Mankush, Chagni, Gidaayana, Gimbi, Angerguten, Nekemte, Gambella, Masha, Aman and Sekoru received more than 30 heavy rainfalls in 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Chefa, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Dalfagi, Nuraira, Semera, Majete, Gewane and Aisha were recorded as 35.0 to 45.4 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 20, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ባቲ፣ ማጀቴ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation in the north, northwest, west, central and south of our country, which benefit from kiremt rains. In connection with this, the northwest, central, east, south and southeast zones of Tigray region; North, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojam, north and south Wollo, Waghkhemra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; Gabi, Fanti and Hari Zones from Afar Region; Assosa, Kamash and Maokomo Zones from Benishangul Gumuz Region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West and East Hararge and West Arsi Zones from Oromia Region; Addis Ababa; Nuer Zone from Gambella Region; The Southwestern Ethiopian Region’s Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; the Central Ethiopian Region’s Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; the Southern Ethiopian Region’s Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedio zones and the Sidama Region’s zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. On the other hand, the highest daily temperature in Samara, Dubti, Bati, Majete, Aisha, Chafra, Elidar, Gwane, Dalifagi and Metahara is recorded above 38 degrees Celsius.