Daily Weather Report 25 June 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ላሊበላ፣ ደ/ ታቦር፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላይበር፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ በደሌ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ ቡሌሆራ፣ አደሌ፣ ቦሬ፣ ኩርፋጨሌ፣ ቁልቢ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ እምድብር፣ ሰኮሩ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ዲላ እና ወላይታ ሶዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጊምቢ፣ አይራ፣ ማሻ እና ፉኝዶ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ዳልፋጊ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ፣ ማጀቴ፣ መተማ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 እስከ 44.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the northwest, west, central and southern regions of our country. In connection with this, there were also clouds in Debark, Metema, Gondar, Aykel, Lalibela, De/ Tabor, Bahir Dar, Chagni, Dangla, Liber, Gambella, Abobo, Fugendo, Gore, Chira, Jimma, Limugenet, Bedele, Angerugut, Nekemte, Arjo, Gidayana, Shambu, Ejaji, Bulehora, Adele, Bore, Kurfachele, Kulbi, Woliso, Addis Ababa, Emdbir, Sekoru, Hosanna, Warabe, Dilla and Wolaita Sodo received light to moderate rainfall. In addition, Gimbi, Aira, Masha and Fugendo received more than 30 heavy rainfalls. On the other hand, the highest daily temperatures in Fundo, Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Awash Arba, Gewane, Kebridehar, Dalifagi, Nuraira, Semera, Majete, Metema and Aisha were recorded as 35.0 to 44.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In connection with this, the Northwest, Central, East, South and Southeast zones of Tigray Region; From the Amhara region, the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo, Waghemra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; from the Benishangul Gumuz region, the Asosa, Kamash, Metekel and Maokomo Zones; From the Oromia Region, the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena and West Arsi; Addis Ababa; from the Gambella Region, the zones of Anuak, Itang, Nuer and Majang; The Southwestern Ethiopian Region’s Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; the Central Ethiopian Region’s Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; the Southern Ethiopian Region’s Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedio zones and the Sidama Region’s zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Additionally, our numerical forecast indicates that some areas of South Gondar, East Gojam, Buno Bedele, East Wellega and West Shewa zones will experience heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperature will be recorded above 38 degrees Celsius in Semera, Dubti, Aisha, Chafra, Elidar, Gewane, Dalifagi and Metahara.