Daily Weather Report 25 June 17

Weather Summary for previous day

June 16, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ ጎንደር፣ ሻሁራ፣ ደ/ ታቦር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ አዴት፣ ደ/ማርቆስ፣ የትኖራ፣ ማንኩሽ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ አርጆ፣ ሻምቡ፣ ጊዳአያና፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሐሮማያ፣ እምድብር፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ማሻ፣ አማን፣ ማጂ እና ሳውላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነጆ፣ ጨዋቃ፣ ነቀምቴ እና ፉኝዶ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር፣ ዳልፋጊ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 እስከ 44.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western, central and northwestern regions of our country had cloud cover. In connection with this, there were also thunderstorms in Debark, Gondar, Shahura, De/Tabor, Chagni, Dangla, Adet, De/Markos, Yetnora, Mankush, Asosa, Gambella, Dembidolo, Gore, Chira, Jimma, Bedele, Arjo, Shambu, Gidayana, Ambo, Woliso, Haromaya, Emdbir, Tepi, Tercha, Masha, Aman, Maji and Saula received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Nejo, Chewaka, Nekemte and Fugendo. On the other hand, the highest daily temperatures in Fundo, Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Mieso, Gewane, Kebridehar, Dalifagi, Nuraira, Samara and Aisha were recorded as 35.0 to 44.8 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 18, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የክረምት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ምዕራብ ጎጃም፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ አሶሳ፣ ካማሽ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow Our numerical forecast indicates that weather events that create favorable conditions for the occurrence of winter rains will intensify. In this regard, the Northwest, Central, East and Southeast zones of Tigray Region; the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo, Waghimra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones of Amhara Region; From Benishangul Gumuz Region: Asosa, Kamash, Metekel and Maokomo Zones; From Oromia Region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West Arsi and West and East Hararge Zones; Addis Ababa; From Gambella Region: Anuak, Itang and Majang Zones; The Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region and the Sidama Region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out winter agricultural activities. In addition, West Gojam, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, Asosa, Kamash, West Shewa, Sheka and Bench Sheko zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the highest daily temperature in Samara, Dubti, Aisha, Chafra, Elidar, Gewane, Dalifagi and Metahara is recorded above 38 degrees Celsius.