Daily Weather Report 25 June 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይከል፣ ጎንደር፣ ዳንግላ፣ ደ/ማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ እንዋሪ፣ መተከል፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ደምብዶሎ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ጊዳአያና፣ ሊሙገነት፣ ጎሬ፣ አምቦ፣ ኢጃጂ፣ በደሌ፣ ጨዋቃ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ አማን፣ ሆሳዕና፣ እምድብር፣ ተርጫ፣ ጨለንቆ እና ሐረር ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቻግኒ፣ ቴፒ እና ማሻ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.5 እስከ 41.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the western, central and northwestern regions of our country had cloud cover. In this regard, Aykel, Gondar, Dangla, De/Markos, Debrework, Enwari, Metekel, Bulen, Asosa, Dembidolo, Gimbi, Aira, Arjo, Gidayana, Limugenet, Gore, Ambo, Ejaji, Bedele, Chewaka, Addis Ababa, Bui, Aman, Hosanna, Emdbir, Tercha, Chelenko and Harar they received light to moderate rainfall, with heavy rainfall of more than 30 cm recorded in Chagni, Tepi and Masha. On the other hand, in Fugendo, Chefa, Bati, Metahara, Dire Dawa, Mieso and Aisha, the maximum daily temperature was recorded as 35.5 to 41.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማዕከላዊ ትግራይ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ካማሽ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ጉራጌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ አሳይታ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of Kiremet rains will be strong in the areas of our country that benefit from Kiremet rains. In this regard, the West, North West, Central, East and South East zones of Tigray Region; the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo, Waghemra and North Shewa zones of Amhara Region; From Benishangul Gumuz Region: Asosa, Kamash, Metekel and Maokomo Zones; From Oromia Region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West Arsi and West and East Hararge Zones; Addis Ababa; From Gambella Region: Anuak, Itang and Majang Zones; The Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region and the Sidama Region zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, our numerical forecast data indicates that Central Tigray, North and South Wollo, Kamash, West Shewa and Gurage zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Semera, Dubti, Asita, Aisha, Chafra, Elidar, Gewane, Dalifagi, Awash Arba and Metahara.