Daily Weather Report 25 June 15

Weather Summary for previous day

June 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ የቄላም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፤ የአኙዋክ ዞን፤ የዳዉሮ ዞን፣ የወላይታ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጨዋቃ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በፉኝዶ፣ መተሀራ እና ድሬዳዋ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over our country's western, central, southern, and eastern parts. In this respect, the north, central, and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, Jimma, Ilubabor, west, southwest, and east Shewa, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa, Dire Dawa; Agnuwak zone, Dawuro zone, Walaita zone and Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, heavy rain of more than 30 mm was recorded in Chewaka. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Fugnido, Metehara and Dire Dawa.

Weather Forecast for next day

June 16, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቀለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና የደቡብ ሶማሌ ደቡባዊ ክፍል ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ መተማ እና ፉኝዶ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud coverage and accumulation over the northwest, west, central, southwest, northeast, and east regions of the country, which are benefit from Kiremt rain. In this regard, the west, north west, central, southeast and east zones of Tigray region; the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Waghemra and north Shewa zones of Amhara region; the Metekal and Kamashi zones of Benishangul Gumuz region; the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Rika, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale, Arsi and west Arsi and west Hararge zones of Oromia region; Majang and Agnuwak zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones of south west Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones of the central Ethiopia region; Walaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones of south Ethiopia region; Sidama region zones and southern part of Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). The amount and distribution of rainfall will be significant for carrying out agricultural activities. Moreover, south Gondar, west Gojjam, west and south west Shewa zones will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature in Samara, Chifra, Dubti, Mile, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, Metema, and Fugnido will be recorded above 38 degrees Celsius.