Daily Weather Report 25 June 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፤ ጋምቤላ፤ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ስዳማ ክልል የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሻሁራ፣ ቻግኒ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ወሊሶ፣ ኢጃጂ፣ አዲስ አበባ፣ ኩሉምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ባሌሮቤ፣ ነገሌ፣ ቦሬ፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳዉላ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ እና ሐዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላ፣ ማሻ እና አማን ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ መተማ፣ መተሀራ እና ድሬዳዋ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.6 እስከ 41.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, west Amhara; Gambella; west, central, south, and east Oromia; Benshangul Gumuz; south west, south, and central Ethiopia, and the Sidama region had cloud coverage. In this regard, Shahura, Chagni, Lare, Abobo, Nekemte, Bedele, Gore, Chira, Jimma, Limugenet, Sokoru, Weliso, Ijaji, Addis Ababa, Kulumsa, Arsirobe, Gelemso, Balerobe, Negele, Bore, Tepi, Tercha, Walaita Sodo, Sawula, Hosaina, Werabe, and Hawassa received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Gambella, Masha, and Aman. On the other hand, the maximum daily temperatures in Fugnido, Metema, Metehara, and Dire Dawa were recorded at 36.6 to 41.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መኖር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ፣ መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፤ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ቆራሔ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ፉኝዶ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, the weather conditions favorable to Kiremt rain will be more intense in the western half, central, southern, and eastern parts of the country. Consequently, from Tigray region the west, north west and central zones; from Amhara region the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Waghemra and north Shewa zones; from Benishangul Gumuz region Kamashi, Metekel and Asossa zones; from Oromia region Ilubabor, Jimma, Buno Bedele, Horro Guduru and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; from Gambella region Majang zone; from south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo; zones of Sidama region and from Somali region Dawa, Korahe, Shebelle and Jarar will have light to moderate rainfall (1-29 mm). Thus, the amount and distribution of rainfall will be significant for functioning agricultural activities. In contrast, the maximum daily temperature will be recorded above 38 degrees Celsius in Metema, Metekel, Fugnido, Chifra, Semera, Dubti, Mile, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, and Metehara.