Daily Weather Report 25 June 13

Weather Summary for previous day

June 12, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም መተማ፣ ማንኩሽ፣ አሶሳ፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ደምብዶሎ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ጨዋቃ፣ ጊምቢ፣ አርጆ፣ ሻምቡ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ወሊሶ፣ አምቦ፣ ኢጃጂ፣ አዲስ አበባ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ጃራ፣ ባሌሮቤ፣ ሐዋሳ፣ ተርጫ፣ ቴፒ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ቡርጅ፣ ጂንካ፣ ቦሬ፣ ቡለሆራ፣ ነገሌ እና ሞያሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ጭፍራ ገዋኔ፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ ኑራኤራ፣ መተሀራ እና ድሬዳዋ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the northwest, west, southwest, central and southern parts of the country. In this respect, Metema, Mankush, Asossa, Lare, Gambella, Fugnido, Dembidolo, Aira, Arjo, Chewaka, Gimbi, Arjo, Shambu, Gidayana, Nekemte, Bedele, Gore, Jimma, Chira, Gatira, Limugenet, Sokoru, Weliso, Ambo, Ijaji, Addis Ababa, Emdibir, Hosaina, Werabe, Jara, Balerobe, Hawassa, Tercha, Tepi, Walaita Sodo, Burji, Jinka, Bore, Bulehora, Negelle and Moyale received light to moderate rainfall. On the other hand, the maximum daily temperature was recorded above 38 degrees Celsius in Metema, Fugnido, Semera, Chifra, Gewane, Aisha, Awash Arba, Nuraera, Metehara, and Dire Dawa.

Weather Forecast for next day

June 14, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ካማሽ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ኤሊዳር፣ አሳይታ፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና መተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, improved cloud coverage and accumulation are expected in the western, central, and eastern parts of the country. Concerning this, from Tigray region the western zone; from Amhara region the west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; the Benishangul Gumuz region’s Metekal, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale, Arsi and west Arsi and east Hararge zones; Addis Ababa; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; the central Ethiopia region’s Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones; the zones of Sidama region and the zones of Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe and Jarar in the Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, Horro Guduru, west and east Wellega, Kamashi, and west Shewa zones will receive heavy rain of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum day temperatures in Chifra, Semera, Dubti, Elidar, Asaita, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, and Metema are expected to be above 38 degrees Celsius.