Daily Weather Report 25 June 12

Weather Summary for previous day

June 11, 2025

በትናንትናው ዕለት በደባርቅ፣ ደብረወርቅ፣ አየሁ፣ ማንኩሽ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ አንገርጉትን፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ ካቺሴ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ እምድብር፣ ወራቤ፣ ቦሬ እና ቴፒ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በጭራ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ ጨፋ፣ ሸዋሮቢት፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና ድሬዳዋ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Debark, Debrework, Ayehu, Mankush, Asosa, Nedjo, Gimbi, Nekemte, Angergutin, Arjo, Gore, Gatira, Jimma, Limugenet, Kachise, Weliso, Addis Ababa, Imdibir, Werabe, Bore, and Tepi had cloud coverage and received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was also recorded in Chira. In contrast, the day's maximum temperature was recorded above 38 degrees Celsius in Semera, Chifra, Gewane, Cheffa, Shewarobit, Aisha, Awash Arba, Metehara, and Dire Dawa.

Weather Forecast for next day

June 13, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ፣ መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል በጥቂት ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ካማሽ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ መተከል፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the upcoming day, the northwest, west, central, southwest, south, and east parts of the country will have cloud coverage. Consequently, the western zone of Tigray region; the western, north and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones of Amhara region; the Kamash, Metekel and Asossa zones of Benishangul Gumuz region; the Ilubabor, Jimma, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa, west Guji, Bale and west Arsi zones of Oromia region; Addis Ababa; the Agnuak and Majang zones of Gambella region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones of south west Ethiopia region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones of the central Ethiopian region; Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo Zones of the south Ethiopian region; Sidama region zones and a few Dawa, Liben, Afder and Shebelle zones of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, Kamashi, west and east Wellega, and south west Shewa zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the numerical weather forecast indicates that the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Metekel, Chifra, Semera, Dubti, Mile, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, and Metehara.