Daily Weather Report 25 June 11

Weather Summary for previous day

June 10, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ ምዕራብ እና ደቡብ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልል የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ አየሁ፣ ደብረወርቅ፣ መተከል፣ ቡለን፣ ደምብዶሎ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ ሊሙገነት፣ ጎሬ፣ ወሊሶ፣ አምቦ፣ ካቺሴ፣ ኢጃጂ፣ አዲስ አበባ፣ አርሲሮቤ፣ ጂንካ፣ ብላቴ፣ ወራቤ እና ሐዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቦሬ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ ጨፋ፣ ሰመራ፣ ባቲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.5 እስከ 45.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in North, West and South Amhara; Benshangul Gumuz; West, Central and South Oromia; Gambella; Central Ethiopia and Sidama Region. In this regard, Debark, Aykel, Bahir Dar, Chagni, Dangla, Ayehu, Debrework, Metekel, Bulen, Dembidolo, Gimbi, Aira, Arjo, Gidayana, Nekemte, Limugenet, Gore, Woliso, Ambo, Kachise, Ejaji, Addis Ababa, Arsi Robe, Jinka, Bilate, Warabe and Hawassa received light to moderate rainfall, while heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Bore. On the other hand, in Fugendo, Gambella, Chefa, Semera, Bati, Gewane, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Mieso and Gode, the maximum temperature of the day was recorded as 35.5 to 45.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 12, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ አንፃራዊ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማዕከላዊ ጎንደር፣ ካማሽ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ አሳይታ፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for rain formation will be relatively strong in the western, southern, central, northwestern, and eastern regions of our country. In addition, the western and northwestern zones of Tigray Region; From the Amhara region, the West, North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam Zones; from the Benishangul Gumuz region, the Asosa, Kamash, Metekel and Maokomo Zones; from the Oromia region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wollega, North, West and South West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, West Arsi and West and East Hararge Zones; Addis Ababa; Anuak and Majang zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedio zones from Southern Ethiopia region; Sidama region zones and In the Somali region, Dawa, Liben, Afder, Erer, Jarar, Shebele, Korahe and Dolo zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, Central Gondar, Kamash, West Wellega and Buno Bedele zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours, our numerical forecast data indicates. On the other hand, the highest daily temperature in Samara, Dubti, Chafra, Elidar, Asita, Aisha, Gwane, Dalifagi, Awash Arba and Metahara will be recorded above 38 degrees Celsius.