Daily Weather Report 25 June 10

Weather Summary for previous day

June 9, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ ምዕራብ እና ደቡብ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ስዳማ ክልል የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ አየሁ፣ ደብረማርቆስ፣ ቡለን፣ ደምብዶሎ፣ አይራ፣ አንገርጉትን፣ አርጆ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ወሊሶ፣ አምቦ፣ ካቺሴ፣ ኢጃጂ፣ አዲስ አበባ፣ አርሲሮቤ፣ ሚኤሶ፣ ቦሬ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ እና ሐዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሻምቡ እና ነጆ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ጨፋ፣ አይሻ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.5 እስከ 42.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, north, west, and south Amhara; Benshangul Gumuz; west, central, and east Oromia; Gambella; central Ethiopia, and Sidama region had cloud coverage. In this regard, Debark, Bahirdar, Chagni, Dangila, Ayehu, Debremarkos, Bulen, Dembidolo, Aira, Angergutin, Arjo, Gidayana, Nekemte, Bedele, Gore, Weliso, Ambo, Kachise, Ijaji, Addis Ababa, Arsirobe, Mieso, Bore, Hosaina, Werabe, and Hawassa received light to moderate rainfall. Besides, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Shambu and Nedjo. On the other hand, the maximum daily temperatures in Fugnido, Cheffa, Aisha, Metehara, Dire Dawa, Mieso, and Gode were recorded as 36.5 to 42.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

June 11, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ ወለጋ፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ኤሊዳር፣ አሳይታ፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ እና መተሀራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, the country's northwest, west, central, south, and southwest parts will have cloud coverage. In line with this, from Tigray region west and northwest zones; from Amhara region west, north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; Benishangul Gumuz region Asossa, Kamashi, Metekel and Mao Komo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west and southwest Shewa, Guji and west Guji, Bale and west Arsi zones; Addis Ababa; Gambella region Agnuak, Majang, Nuwer and Itang zones; from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the South Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Dawa and Liben zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, east Wellega, Jimma, Buno Bedele, and southwest Shewa zones will experience heavy rain of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature will be recorded exceeding 38 degrees Celsius in Metema, Metekel, Chifra, Semera, Dubti, Elidar, Asaita, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, and Metehara.