Daily Weather Report 25 July 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬእንደሥላሴ፣ አይደር፣ መቀሌ፣ ፍረወይኒ፣ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ ባህርዳር፣ መተማ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ደብረ ወርቅ፣ ነፋስ መውጫ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ደብረታቦር፣ ባቲ፣ ጉንዶ መስቀል፣ እንዋሪ፣ አለም ከተማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ወግዲ፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላል፣ ደበል፣ ደነባ፣ ጅሩ፣ መንዲዳ፣ ሮቢት፣ ጊሽራቤል፣ ግንደበረት፣ ጫጫ፣ ድልብ፣ ላሊበላ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ ሻምቡ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ቦርቃ፣ ፉጎሌቃ፣ ኦሞናዳ፣ ያዮ፣ ቢላምቢሎ፣ ሀሮ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ ባቱ፣ ሁንቴ፣ ሳጉሬ፣ መራሮ፣ ቦሬ፣ ፣ ሀዋሳ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ወራቤ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጊዳአያና፣ ጊምቢ፣ በደሌ፣ ሰኮሩ፣ ቡኢ፣ ጅሩ፣ ደራ እና ያዮ በ24 ሰዓት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefit from the kiremt rains. In connection with this, there were heavy rains in ShireendaSelassie, Ayder, Mekelle, Freweini, Gondar, Debark, Bahir Dar, Metema, Aykel, Shahura, Chagni, Dangla, Mota, Debre Work, NeifsMewecha, Debre Markos, Yetenora, Debretabor, Bati, Gundo Cross, Enwari, Alem City, Debre Berhan, Wegdi, Debresina, Gashena, Molal, Debel, Deneba, Jiru, Mendida, Robit, Gishrabel, Gendeberet, Chata, Dlab, Lalibela, Khafa, Mekenselam, Wereilu, Mehalmeda, Shambu, Gore, Jimma, Borqa, Fugoleqa, Omonada, Yayo, Bilambilo, Haro, Ijaj, Wolisso, Bishoftu, Batu, Hunte, Sagure, Meraro, Bore, Hawassa, Masha, Tercha, Warabe and Addis Ababa received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Gidaayana, Gimbi, Bedele, Sekoru, Bui, Jiru, Dera and Yayo in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ደላንታ፣ አምባሰል፣ ኩታበር፣ ለጋምቦ፣ ግሽራቤል፣ ደብረወርቅ፣ እናርጅ እናውጋ፣ ቢቸና፣ ጣርማበር፣ ደብረሲና፣ ቀወት፣ ሞላሌ፣ ሸኖ፣ ሊሙ ኮሳ፣ ኦሞናዳ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow There will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremt rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West Hararge and Bale zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Asosa, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang, Itang and Anwak zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Yem liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Sidama region zones and Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones from Afar region and from Somali Region City Zone will experience light to moderate rainfall in many areas. In addition, due to the strengthening weather events, Lalibela, Wogeltiye, Delanta, Ambassel, Kutaber, Legambo, Geshrabel, Debrework, Enarj Enawga, Bichna, Tarmaber, Debresina, Kewet, Molale, Sheno, Limu Kosa, Omonada and Addis Ababa will experience heavy rainfall that could cause flash flooding within 24 hours.