Daily Weather Report 25 July 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአድዋ፣ አፅቢ፣ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ደብረታቦር፣ አዲስዘመን፣ መካነኢየሱስ፣ ቡሬ፣ ሊበን፣ መርጦለማርያም፣ ረቡገበያ፣ መርሳ፣ ሀይቅ፣ ጉጉፍቱ፣ ወግዲ፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላል፣ ደበል፣ ደነባ፣ ጅሩ፣ መንዲዳ፣ ሮቢት፣ ጊሽራቤል፣ ግንደበረት፣ ጫጫ፣ ድልብ፣ አልየአምባ፣ ላሊበላ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ ሻምቡ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ቦርቃ፣ ፉጎሌቃ፣ ኦሞናዳ፣ ያዮ፣ ቢላምቢሎ፣ ሀሮ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ ፊንጫ፣ አዲስዓለም፣ ሀሮዶየ፣ ባቱ፣ ሁንቴ፣ ሳጉሬ፣ መራሮ፣ ዲንሾ፣ ዶዶላ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ሂርና፣ መልካጀብዱ፣ ሀዋሳ፣ ማሻ፣ አማን፣ ተርጫ፣ አሽ፣ ባሮቦንጋ፣ ቅ/ ገበያ፣ ኮበን፣ኩሚ፣ መንገሽ፣ አቢጃራ፣ ወራቤ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ኩሉምሳ፣ አማን፣ መንደር 11፣ አቦመሪጋ እና ጭልቦ መንደር በ24 ሰዓት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In this regard, Adwa, Atsbi, Gondar, Debark, Bahir Dar, Chagni, Dangla, Mota, Debre Markos, Enoora, Debre Tabor, Addiszemen, Mekanyesus, Bure, Liben, Mertole Mariam, Rebuketa, Mersa, Hayq, Gugufutu, Wagdi, Debresina, Gashena, Molal, Debel, Denba, Jiru, Mendida, Robit, Gishrabel, Gendeberet, Chacha, Dlib, Alyamba, Lalibela, Chefa, Mekaneslam, Wereilu, Mehalmeda, Shambu, Gore, Jimma, Borqa, Fugoleka, Omonada, Yayo, Bilambilo, Haro, Ijaj, Wolisso, Bishoftu, Fincha, Addisalem, Harodoye, Batu, Hunte, Sagure, Meraro, Dinsho, Dodola, Bulehora, Bore, Hirna, Melkajebdu, Hawassa, Masha, Aman, Tarcha, Ash, Barobonga, Q/Gebeye, Koben, Kumi, Mengesh, Abijara, Warabe, Dire Dawa and Addis Ababa received light to moderate rainfall. In addition, Gambella, Nekemte, Bedele, Mkuru, Kulumsa, Aman, Village 11, Abomeriga and Chelbo Village received heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የመኸር የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በማይካድራ፣ ዳንሻ፣ ማይጋባ፣ ሽራሮ፣ እንዳባጉና፣ ሐውዜን፣ አክሱም፣ የጭላ፣ አድዋ፣ አዲግራት፣ መቀሌ፣ አይደር፣ ሳምረ፣ አዲጉዶም፣ አመያ፣ ጎሮ፣ ወንጪ፣ ወሊሶ፣ ወልቂጤ፣ እንድብር፣ ደጫ፣ ጨና፣ ዋጫ፣ ጋጪ እና ሚዛን አማን በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of kiremet rains will be more intense in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, Central, West and South Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang, Anuak and Itang zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawro and West Omo zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, YEM liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out harvest agricultural activities and for providing fodder and drinking water to pastoral areas. Additionally, Mayikadra, Dansha, Maygaba, Shiraro, Endabaguna, Hawzen, Aksum, Yecla, Adwa, Adigrat, Mekelle, Ayder, Samre, Adigudom, Amaya, Goro, Wenchi, Wolisso, Welkite, Endibr, Decha, Chena, Wacha, Gachi and Mizan Aman will experience heavy rainfall within 24 hours.