Daily Weather Report 25 July 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ አባይሸለቆ፣ ደብረታቦር፣ አዲስዘመን፣ መካነኢየሱስ፣ ቡሬ፣ ሊበን፣ መርጦለማርያም፣ ረቡገበያ፣ ሸዲ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ መርሳ፣ ሀይቅ፣ ደጋን፣ ጉጉፍቱ፣ አቀስታ፣ ወግዲ፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላል፣ ደበል፣ ደነባ፣ ጅሩ፣ መንዲዳ፣ ሮቢት፣ ጊሽራቤል፣ ግንደበረት፣ ጫጫ፣ ድልብ፣ አልየአምባ፣ ላሊበላ፣ ስሪንቃ፣ አምባማርያም፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ ደብረብርሀን፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ቦርቃ፣ ፉጎሌቃ፣ ኦሞናዳ፣ ያዮ፣ ቢላምቢሎ፣ ሀሮ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ቢሾፍቱ፣ ፊንጫ፣ አዲስዓለም፣ ሀሮዶየ፣ ባቱ፣ ሁንቴ፣ ሳጉሬ፣ መራሮ፣ ዲንሾ፣ ዶዶላ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ሂርና፣ መልካጀብዱ፣ ሀዋሳ፣ ማሻ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ኩሚ፣ አሽ፣ ሙጊ፣ ወራቤ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፓዌ እና አሶሳ በ24 ሰኣት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northeast, northwest, central, east, southwest, and south parts of our country. In this regards, cloud cover was observed over Mekelle, Aykel, Shahura, Bahir Dar, Chagni, Dangla, Motta, Debrework, Debre Markos, Yetnora, Abay Shelleko, Debretabor, Addis Alem, MekaneEeysus, Bure, Liben, Mertolemariam, Erobgebeya, Shedi, Combolcha, Bati, Mersa, Haik, Degan, Guguftu, Akesta, Wegdi, Debresina, Gashena, Mollale, Debel, Deneba, Jiru, Mendida, Robit, Gishrabel, Gindeberet, Chacha, Amba Mariam, Cheffa, Mekansalam, Wereilu, Mehalmeda, Debrebrihan, Nekemte, Shambu, Bedele, Gore, Jimma, Borka, Fugoleka, Omonada, Yayo, Bilambilo, Haro, Ejaji, Woliso, Fiche, Bishoftu, Fincha, Addis Alem, Harodoye, Batu, Hunte, Sagure, Meraro, Dinsho, Dodola, Bulehora, Bore, Hirna, Melekjbidu, Hawassa, Masha, Aman, Tercha, Gambella, Fugnido, Kumi, Ashi, Mugi, Werabe, Dire Dawa, and Addis Ababa received light to moderate rainfall. Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Pawe and Asossa within a 24-hour.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የመኸር የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በቡግና፣ መቄት፣ ላስታ፣ አንጎት፣ ታችጋንት፣ ጓንጓ፣ ባንጃ፣ ቦቶርጦላይ፣ ሶኮሩ፣ የም፣ አበሽጌ፣ ቸሃ እና ቸታ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, our numerical forecast indicates that there will be strong cloud cover and accumulation over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray region; From the Amhara region, North, West and South Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; From Benishangul Gumuz Region, Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel zones; from Gambella Region, Majang, Agnuak and Itang zones; from Southwestern Ethiopia Region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and West Omo zones; from Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; all zones of Sidama Region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; from Southern Ethiopia region Siti and Fafen zones; and from south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, South Omo and Basketo zones will receive light to moderate rainfall in many areas. The distribution and amount of rainfall will be crucial for conducting Meher agricultural activities and for pasture and drinking water in pastoral areas. Additionally, there will be heavy rainfall that may lead to flash flooding within a 24-hour in Bugna, Meket, Lasta, Angot, Tachgaynt, Guangua, Banja, Botortolai, Sokoru, Yem, Abeshige, Cheha, and Cheta.