Daily Weather Report 25 July 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬእንደሥላሴ፣ ደንጎላት፣ መቀሌ፣ አፅቢ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ውቅሮ፣ መኾኒ፣ ወርቅ ማረይ፣ ፅጌረዳ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ አዴት፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ረቡገበያ፣ መርጦ ለማርያም ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ቁንዝላ፣ ሸንዲ፣ ኮሶበር፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላሌ፣ወግዲ፣ ደበል፣ ደነባ፣ መንዲዳ፣ ጫጫ፣ አልይአምባ፣ ጊምቢ፣ ቡኢ፣ ቦሬ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ አቃቂ፣ አዲስዓለም፣ ሀሮዶየ፣ አታንጎ፣ ኦሞናዳ፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ሐሮ፣ ሸቤ፣ ቡልቡል፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ባሮቦንጋ፣ ትንሹ ሚጢ፣ ጭንቦ መንደር7፣ ተርጫ፣ ወራቤ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ ቢላቴ፣ ምዕራብአባያ፣ ዲላ፣ እምድብር፣ ይርጋለም፣ ወልበርግ፣ ቡልቂ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በኮምቦልቻ፣ ደ/ ወርቅ፣ ሐይቅ፣ ጉጉፍቱ፣ ቡለን፣ ላሬ እና መንደር 11 በ24 ሰዓት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In this regard, in Shireendu Selassie, Dingolat, Mekele, Atsbi, Ayder, Maichew, Hukro, Mekhoni, Work Marey, Tsigereda, Debarq, Gondar, Aikel, Bahir Dar, Dangla, Mota, Adet, Debre Markos, Tnora, Rebuketa, Merto Lemariam, Mekane Yesus, Kunzla, Shendi, Kosober, Debresina, Gashena, Molale, Wagdi, Debel, Denba, Mendida, Chacha, Alyamba, Gimbi, Bui, Bore, Aira, Nekemte, Shambu, Bedele, Mukur, Gore, Ijaj, Ambo, Wolisso, Kulmsa, Arcirobe, Gelemso, Chelenko, Kulubi, Akaki, Addisalem, Harodoye, Atango, Omonada, Agaro, Bilambilo, Haro, Shebe, Bulbul, Metu, Gambella, Fugendo, Barobonga, Tinishu Mitti, Chilbo Village7, Tercha,Warabe, Wolaytasodo, Saula, Jinka, Bilate, West Abaya, Dilla, Emdbir, Yirgalem, Wolberg, Bulqi and Addis Ababa received light to moderate rainfall. In addition, Kombolcha, De/Work, Hayq, Gugufutu, Bulen, Lare and Village 11 received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዛይ፣ ደምቢ፣ ካማሺ፣ ሆሩ፣ ሻምቡ፣ ሆሩ ቡልቂ፣ ኢፋታ፣ አምቦ ዙርያ፣ ግንደበረት፣ ሜታ ሮቢ፣ ጀልዱ፣ ወንጪ፣ ሊሙ ሴቃ፣ ጮራ፣ ደዴሳ፣ ሱርማ፣ ማጂ እና በ አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ።
Tomorrow Forecast data indicate that weather conditions that create favorable conditions for the occurrence of kiremet rains will intensify in the areas of our country that benefit from Kiremet rains. In this regard, the Central, Northwestern, Southeastern, Southern and Eastern zones of the Tigray region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Benishangul Gumuz Region: Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel Zones; Gambella Region: Majang, Nuer, Agnuak and Itang Zones; Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawro and West Omo Zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, YEM liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; All zones of Sidama Region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; the Siti and Fafen zones of the Somali region; and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, statistical forecast data indicates that heavy rainfall that may cause flash floods will occur in Zai, Dembi, Kamashi, Horu, Shambu, Horu Bulki, Ifata, Ambo Zuria, Gendeberet, Meta Robi, Jeldu, Wenchi, Limu Seka, Chora, Dedesa, Surma, Maji and Addis Ababa within 24 hours.