Daily Weather Report 25 July 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ መካከለኛውና ምስራቅ አማራ፣ ምዕራብና መካከለኛ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ አዴት፣ ደ/ ወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ስሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ እንዋሪ፣ ደ/ ብርሃን፣ ሾላ ገበያ፣ ቡኢ፣ ቦሬ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ባሌሮቤ፣ ጋምቤላ፣ ጌቻ፣ ተርጫ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ ዲላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ብላቴ፣ ሆሳዕና፣ እምድብር እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በኦንጋ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over parts of our country in Western, Central and Eastern Amhara, Western and Central Oromia, Gambella, Central Ethiopia, Southern Ethiopia and Sidama. In this regard, in Aikel, Shahura, Bahir Dar, Dangla, , Adet, De/Work, Debremarkos, Tnora, Lalibela, Wogeltiye, Sringa, Kombolcha, Enwari, De/Birhan, Shola Gebeya, Bui, Bore, Nekemte, Gore, Ijaj, Ambo, Wolisso, Balerobe, Gambella, Gecha, Tercha, Saula, Jinka, Dilla, West Abaya, Blate, Hosanna, Emdbir and Addis Ababa received light to moderate rainfall, while heavy rainfall was recorded in Onga.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በስሬ፣ ጀጁ፣ መርቲ፣ ጉና፣ ሀዊ ጉዲና፣ አጋርፋ፣ ደራ፣ አዳማ፣ ጎሎልቻ፣ ሰዴ፣ ቦሰቴ፣ አዳአ፣ ዱግዳ እና ቢሾፍቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow Our numerical forecast indicates that there will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from Kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West and South Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; From Benishangul Gumuz Region, Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel zones; from Gambella Region, Majang, Agnuak and Itang zones; from Southwestern Ethiopia Region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and West Omo zones; from Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, Yem liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; all zones of Sidama Region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; the Siti and Fafen zones of the Somali region; and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, due to the intensifying weather events, Sere, Jeju, Merti, Guna, Hawi Gudina, Agarfa, Dera, Adama, Gololcha, Sede, Bossete, Adaa, Dugda and Bishoftu will experience heavy rainfall within 24 hours.