Daily Weather Report 25 July 19

Weather Summary for previous day

July 18, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ መተማ፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ አዴት፣ ደ/ ወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ላሊበላ፣ ፅፅቃ፣ ወገልጤና፣ ስሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ መሃልሜዳ፣ ወረኢሉ፣ እንዋሪ፣ ደ/ ብርሃን፣ ሾላ ገበያ፣ ቡኢ፣ ቦሬ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቁልምሳ፣ ገለምሶ፣ ቁልቢ፣ ኦሞናዳ፣ ቢላምቢሎ፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ቅ/ ገበያ፣ ኪሚ፣ ላሎ ቂላ፣ ተርጫ፣ ወራቤ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the winter rains. In connection with this, there were also rains in Mekelle, Gondar, Debark, Metema, Bahir Dar, Dangla, Mota, Adet, De/Work, Debre Markos, Yetenora, , Lalibela, Tsitsika, Wogeltiyna, Srinka, Kombolcha, Mahmeda, Wereilu, Enwari, De/Birhan, Shola Gebeya, Bui, Bore, Aira, Nekemte, Bedele, Chira, Gore, Ejaj, Ambo, Woliso, Kulmsa, Gelemso, Kulbii, Omonada, Bilambilo, Metu, Gambella, K/Gebeya, Kimi, Lalo Qila, Tercha, Warabe, Wolaytasodo, Saula, Jinka, Dilla and Addis Ababa received light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

July 20, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የመኸር የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጉባ፣ ወምበራ፣ ዳንጉር፣ ሸርኮሌ፣ ባምባሲ፣ መንዲ፣ ጉሊሶ፣ አይራ፣ ሰተማ፣ ኦሞናዳ፣ ኮንታ ኮይሻ፣ ማጂ፣ ሱርማ፣ ቦዲቲ፣ ሶዶ ዙርያ፣ ብላቴ፣ ስሬ እና አዳማ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of winter rains will be more intense in the areas of our country that benefit from winter rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Benishangul Gumuz Region: Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel Zones; Gambella Region: Majang, Nuer and Itang Zones; Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawro and West Omo Zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, Yem liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; All zones of Sidama Region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; the Siti and Fafen zones of the Somali region; and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. The amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out agricultural activities in the fall and for providing livestock feed and drinking water in pastoral areas. Additionally, due to the intensifying weather events, Guba, Wombera, Dangur, Sherkole, Bambasi, Mendi, Guliso, Aira, Setema, Omonada, Konta Koisha, Maji, Surma, Boditi, Sodo Zuria, Bilate, Sire and Adama will experience heavy rainfall that may cause flash floods within 24 hours.