Daily Weather Report 25 July 18

Weather Summary for previous day

July 17, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬእንደሥላሴ፣ ደንጎላት፣ እንዳባጉና፣ ፅጌረዳ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ አዴት፣ ደ/ ወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ረቡገበያ፣ መርጦ ለማርያም ፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላሌ፣ ደበል፣ ደነባ፣ መንዲዳ፣ ጊሽራቤል፣ ጫጫ፣ አልይአምባ፣ ጊምቢ፣ ቡኢ፣ ቦሬ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ መቂ፣ አዲስዓለም፣ ሀሮዶየ፣ አታንጎ፣ ኦሞናዳ፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ሐሮ፣ ሸቤ፣ ቡልቡል፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ አሽ፣ አባጃራ፣ ሙጊ፣ ኦንጋ፣፣ ቅ/ ገበያ፣ ተርጫ፣ ወራቤ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ ቢላቴ፣ ምዕራብአባያ፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቢሾፍቱ፣ ሆሳዕና፣ ሳውላ፣ አቃቂ፣ ኩሚ፣ ደራ፣ አትጋጎ እናያንፋን በ24 ሰዓት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the areas of our country that benefited from the kiremet rains had cloud cover over them. In this regard, in Shireenda Selassie, Dingolat, Endabaguna, Tsigereda, Debark, Gondar, Aikel, Bahirdar, Dangla, Mota, Adet, De/Work, Debremarkos, Yetnora, RebuGebeya, Merto leMaryam, Debresina, Gashena, Molal, Debel, Denba, Mendida, Gishrabel, Chacha, Alyamba, Gimbi, Bui, Bore, Aira, Nekemte, Shambu, Bedele, Chira, Gore, Ijaj, Ambo, Wolisso, Kulmsa, Arcirobe, Gelemso, Chelenko, Kulubi, Meki, Addisalem, Harodoye, Atango, Omonada, Agaro, Bilambilo, Haro, Shebe, Bulbul, Metu, Gambella, Ash, Abajara, Mugi, Onga,, Q/ Gebeya, Tercha, Warabe, Wolaytasodo, Saula, Jinka, Bilate, West Abaya, Dilla and Addis Ababa received light to moderate rainfall. In addition, Bishoftu, Hosanna, Saula, Akaki, Kumi, Dera, Atgago and Yanfan received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.

Weather Forecast for next day

July 19, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታ የመፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጋሸና፣ ዋድላ፣ ዳውንት፣ አቅስታ፣ መሃል ሳይንት፣ መካነሰላም፣ ለጋምቦ፣ ቢቸና፣ ደብረወርቅ፣ እናርጅእናውጋ፣ ሁለትእጅ እነሴ፣ ግንደበረት፣ ሜታ ሮቢ፣ ወልመራ፣ አዳበርጋ፣ አዲስ አለም፣ ሰኮሩ፣ ሊሙ ሴቃ፣ ኖኖ ቤንጃ፣ ጮራ፣ ወይራዲጆ፣ ቱርሚ፣ ሀመር እና ዳሰነች በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Forecast data indicates that weather conditions conducive to rain will continue to strengthen. In this regard, the Central, Northwestern, Southeastern, Southern and Eastern zones of Tigray Region; and Amhara Region, From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang, Nuer and Itang zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawro and West Omo zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Yem liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; the Siti and Fafen zones of the Somali region; and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, due to the intensifying weather events, heavy rainfall that may cause flash floods will occur in Gashena, Wadla, Daunt, Aqsta, Mid-Saint, Mekaneslam, Legambo, Bichna, Debrework, Enarjeenauga, Binaye Ense, Gendeberet, Meta Robi, Wolmera, Adaberga, Addis Alem, Sekoru, Limu Seqa, Nono Benja, Chora, Weyradijo, Turmi, Hamer and Dasenach within 24 hours.