Daily Weather Report 25 July 15

Weather Summary for previous day

July 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬእንደሥላሴ፣ አድዋ፣ አዲግራት፣ መቀሌ፣ ሰንቃጣ፣ አጽቢ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ እንዳቡጉና፣ ማይሃንሰ፣ ውቅሮ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ አባይሸለቆ፣ አዲስዘመን፣ አሸር፣ ሊበን፣ ረቡገበያ፣ ኮምቦልቻ፣ ሀይቅ፣ ደጋን፣ ጉጉፍቱ፣ አቀስታ፣ ሰቆጣ፣ ወግዲ፣ ደብረሲና፣ ጋሸና፣ ሞላል፣ ደበል፣ ደነባ፣ ጅሩ፣ መንዲዳ፣ ሮቢት፣ ጊሽራቤል፣ ግንደበረት፣ ጫጫ፣ ግናገር፣ ሪቂ፣ አልይአምባ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽአርባ፣ ኤሊዳር፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ካችሴ፣ ፍቼ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ መተሀራ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ፊንጫ፣ ጨፋዶንሳ፣ አቃቂ፣ አዲስዓለም፣ ሀሮዶየ፣ አታንጎ፣ ቦርቃ፣ ፉጎሌቃ፣ ኦሞናዳ፣ ጎሎልቻ፣ ሁንቴ፣ ሳቡሬ፣ ሳህሉ፣ መራሮ፣ ቀርሳ፣ አሳሳ፣ ዶዶላ፣ ጋምቤላ፣ አሽ፣ ባሮቦንጋ፣ ቅ/ገበያ፣ ላሉቂል፣ ሙጊ፣ ኦንጋ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ማጅ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ ቢላቴ፣ ምዕራብአባ፣ ዲላ እና አይሻ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአማን፣ በኑራኤራ፣ በቦሬ፣ በይረጋጨፌ እና በያፋን በ24 ሰኣት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud coverage across the northeastern, western, central, eastern, and southern parts of our country. In this regards, in Shire, Adwa, Adigrat, Mekelle, Senkata, Atsebi, Aider, Maichew, Abuguna, Mai Hanse, Wukero, Debark, Gondar, Aykel, Shahura, Bahir Dar, Chagni, Dangla, Motta, Debrework, Debre Markos, Yetnora, Abayshelleko, Addis Zemen, Asher, Liben, Erobgebeya, Combolcha, Haik, Degan, Guguftu, Akesta, Sekota, Wegdi, Debresina, Gashena, Mollale, Debel, Deneba, Jiru, Mendida, Robit, Gishrabel, Gindeberet, Chacha, Ginager, Riki, Ali amba, Dalifage, Awasharba, Elidar, Gimbi, Aira, Nekemte, Shambu, Kachise, Fiche, Debel, Chira, Jimma, Ejaji, Ambo, Woliso, Bishoftu, Adama, Metehara, Kulumsa, Arsirobe, Gemelso, Gelemso, Kulubi, Fincha, Chefedonsa, Akaki, Abdisalam, Harodoye, Atango, Borka, Fugoleka, Omonada, Gololcha, Hunte, Sabure, Sahlu, Meraro, Keresa, Assasa, Dodola, Gambella, Ashi, Barobonga, K/Gebeya, Lalukil, Mugi, Onga, Masha, Tercha, Maji, Endibir, Hosana, Werabe, Wolaitasodo, Sawla, Jinka, Bilate, Mirababaya, Dilla, Aisha and Addis Ababa received light to moderate rainfall. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours was recorded in in Aman, Nuraera, Bore, Yirgacheffe and Yafan.

Weather Forecast for next day

July 16, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአዳርቃይ፣ ደባርቅ፣ ደጀን፣ አዋበል፣ አነደድ፣ ጉድሩ፣ አባቦ፣ ጊምቢ፣ ሃሩ፣ ኖሌካባ፣ ሳዪኖሌ፣ ሆማ፣ አልጌሳች፣ ዳሪሙ፣ ጌራ፣ ሸቤሻምቦ፣ ደዶ፣ ገዋታ፣ ጊምቦ፣ አደያኦ፣ ደቻ፣ ቱሎ፣ መንገሽ፣ አመያ ዙሪያ፣ ቸና፣ ቢቲ፣ ዳኖ፣ ኖኖ፣ ኢሉገላኔ፣ ጂባጥ፣ ቸሊያ፣ አመያ፣ ወንጭ፣ ዳኖ፣ ኢሉ፣ ቶሌ፣ ጎሮ፣ ሙሎ፣ ሱሉልታ፣ ውጫሌ፣ ጅዳ፣ ቅምብቢት፣ አዲስ አበባ እና ሲሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will intensify over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awusi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti and Fafen zones; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Kamashi, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang, Itang, Nuwer and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, Kore, and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. Additionally, heavy rainfall that could lead to flash flooding is expected within 24 hours in the areas of Adarkay, Debark, Dejen, Awabel, Aneded, Gudru, Ababo, Gimbi, Haru, Nolekaba, Sainole, Homa, Algesach, Darimu, Gera, Shebeshambu, Dedo, Gawata, Gimbo, Adeyao, Decha, Tullo, Mengsh, Amaya Zuriya, Chena, Bitti, Dano, Nono, Ilu Gelane, Jibat, Chelia, Amaya, Wenchi, Dano, Ilu, Tole, Goro, Mulo, Sululeta, Wichale, jida, Kimbibite, Addis Ababa and Sire. Thus, the Ethiopian Meteorology Institute recommends that the community and relevant authorities take the necessary precautions in areas vulnerable to flooding.