Daily Weather Report 25 July 13

Weather Summary for previous day

July 12, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ደ/ታቦር፣ ነፋስመውጫ፣ ሞጣ፣ ደ/ወርቅ፣ የትኖራ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ አምባ ማርያም፣ ባቲ፣ ወረኢሉ፣ መሃልሜዳ፣ አለምከተማ፣ እንዋሪ፣ ደ/ብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ቡለን፣ ሻምብ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ኑራኤራ፣ መተሀራ፣ ኩልምሳ፣ ገለምሶ፣ ባቱ፣ ጃራ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ አርባምንጭ፣ ጅንካ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ ተርጫ፣ ማሻ፣ ጋምቤላ እና ፉኝዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ፣ በካችሴ፣ በቦሬ እና በቅዳሜገበያ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover over the western half, central, northeastern, eastern, and southern parts of our country. In this regard, in Debark, Aykel, Bahir Dar, De/Tabor, Nefasmewicha, Motta, De/Work, Yetnora, Chagni, Dangla, Lalibela, Amba Maryam, Bati, Wereilu, Mehalmeda, Alemketama, Enwari, De/Berhane, Sholagebeya, Bullen, Shambu, Gore, Jimma, Woliso, Addis Ababa, Adama, Bishoftu, Nuraera, Metehara, Kulumsa, Gelemso, Batu, Jara, Negele, Yabelo, Emdibir, Hosanna, Werabe, Hawassa, Wolaitasodo, Sawla, Arba Minch, Jinka, Konso, Dilla, Tercha, Masha, Gambella, and Fugnido received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Nekemte, Kachise, Bore and Kidamegebeya.

Weather Forecast for next day

July 14, 2025

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በታንኳ መላሼ፣ ሳሃረቲ፣ ላይጋይንት፣ ሁለትእጅነሴ፣ ሰዳ፣ ቢቡኝ፣ ባሶናወረና፣ ሙሎ፣ ሱሉለታ፣ አዲስ አበባ፣ አዳበርጋ፣ ጀልዱ፣ ደንዲ፣ ኖኖ፣ ወንጭ፣ ዳኖ፣ ኢሉ፣ ሰበታ ሀዋስ፣ አቃቂ፣ ሳሲጋ፣ ለካዱለቻ፣ አርጆ፣ ኖኖብንጂ፣ ሊሙሰቃ፣ ጮራ፣ ጨዋቃ፣ ዳቦሃና፣ እነሞር፣ ቸሃ፣ አዳሚቱሉ፣ ዱግዳ፣ ዶዶታ፣ መዘንጊ እና ካማሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, the rain-giving weather events will intensify over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awusi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti zone; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Kamashi, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang, Itang, Nuwer and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. In addition, there will be heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours in Tankua Melashe, Sahareti, Laygaynt, HuletEjnese, Sedae, Bibougne, Bassona Werna, Mulo, Sululeta, Addis Ababa, Adaberga, Jeldu, Dendee, Nono, Wenchi, Dano, Ilu, Sebata Hawassa, Akaki, Sasiga, Lekadulecha, Arjo, Nonobnji, Limmuseka, Chora, Chewaka, Dabo Hana, Enemor, Cheha, Adamitulu, Dugda, Dodota, Mezenga, and Kamashi are expected to experience heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour. On the other hand, the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Samara, Dubti, Mille, Elidar, Aisha, Chifra, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, and Kebridehar.