Daily Weather Report 25 July 12

Weather Summary for previous day

July 11, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሻሁራ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ነፋስ መውጫ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ስሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ መሀልሜዳ፣ መካነሰላም፣ ደ/ወርቅ፣ ደ/ማርቆስ፣ የትኖራ፣ አለምከተማ፣ እንዋሪ፣ ደ/ብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ጉንዶመስቀል፣ ፍቼ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ አዲስ አበባ፣ ወሊሶ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ጎሬ፣ ደምቢዶሎ፣ ኩልምሳ፣ ባቱ፣ አደሌ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ቡሌሆራ፣ ገለምሶ፣ ኩርፋጨሌ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ትንሹ ሚጢ፣ ኦንጋ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ቡኢ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ቢላቴ፣ ጅንካ፣ ኮንሶ እና በዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሞጣ እና በአይከል ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ እና በመልካጀብዱ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud coverage over the western half, central, northeastern, eastern, and southern parts of our country. In this regards, in Shahura, Chagni, Dangla, Nefas Mewcha, Lalibela, Wogeltena, Sirinka, Combolcha, Mehalmeda, Mekansalam, De/Work, De/Markos, Yetnora, Alemketama, Enwari, De/Berhane, Sholagebeya, Gundomeskel, Fiche, Nekemte, Shambu, Addis Ababa, Woliso, Adama, Jimma, Gore, Dembidolo, Kulumsa, Batu, Adelle, Bore, Bore, Negele, Moyale, Bulehora, Gelemso, Kurfachele, Dire Dawa, Gambella, Abobo, Tinshu Mitti, Onga, Masha, Tercha, Bui, Endibir, Hosanna, Werabe, Hawassa, Wolaitasodo, Bilate, Jinka, Konso, and Dilla received light to moderate amounts of rainfall, while heavy amounts of rainfall were recorded in Motta and Aykel. Conversely, the maximum temperature of the day was recorded in Dire Dawa and Melekjbidu, exceeding 35.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

July 13, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በምዕራብ አጋማሽ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ በረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን እና ጃራር ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በለጋምቡ፣ ለገሂዳ፣ ቡግና፣ ቀወት፣ ጣርማበር፣ አንኮበር፣ አሳግርት፣ ደባይጠላት፣ ወሊሶ፣ ጎሮ(ሸዋ) ቶሌ፣ ሊበንጭቋላ፣ ቦራ፣ ዱግዳ፣ ባቱ፣ አርሲነገሌ፣ ዳሎቻ፣ ስልጤ፣ በርበር፣ እዣ፣ ቸሀ፣ እነሞር፣ ጊቤ፣ የም፣ ኦሞናዳ፣ ሴካጨኮርሳ፣ ጌራ፣ ሁምቤ እና ሎካአባያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, There will be strong cloud cover and accomplish over the Kiremt rain benefiting areas of western half, northeastern, central, eastern, southern, and southwestern parts of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji, and west Guji, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti zone; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Kamashi, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang zone; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, Kore, Gardolla and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. In addition, Legambu, Legehida, Bugna, Kewet, Tarmaber, Ankober, Asagart, Debaytglat, Woliso, Goro (Shewa), Tole, Liben Chukala, Bora, Dugda, Batu, Arsi Negele, Dalocha, Silte, Berber, Ezza, Cheha, Enmor, Gibe, Yem, Omonada, Sekachekorsa, Gera, Humbe, and Lokeabaya are expected to experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Samara, Dubti, Mille, Elidar, Aisha, Chifra, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Metehara, and Kebridehar.