Daily Weather Report 25 July 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ አዲግራት፣ ሽሬእንዳስላሴ፣ አድዋ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ፍረወይኒ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መሀልሜዳ፣ መካነሰላም፣ ጉንዶመስቀል፣ አለም ከተማ፣ እንዋሪ፣ ደ/ብርሃን፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ በደሌ፣ አርጆ፣ ጭራ፣ ኢጃጂ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ወሊሶ፣ ቡኢ፣ አዳማ፣ ኑራኢራ፣ አቦምሳ፣ ባሌሮቤ፣ ጃራ፣ ጊንር፣ ሂርና፣ ጨለንቆ፣ ሀረር፣ አዲስ አበባ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ እምድብር፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ብላቴ፣ ሳውላ፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ ምዕራብ አባያ፣ ዲላ፣ ቡርጂ፣ ጨፌ ዶንሳ፣ ሆሮዶዮ፣ አቃቂ፣ ፊንጫ፣ አሺ፣ ጉበቲ፣ ቡሬ፣ ፈረስቤት፣ ረቡዕ ገበያ፣ ሸንዲ፣ መካነ ኢየሱስ፣ አትናጎ፣ መቱ፣ ጎሎልቻ፣ ኣሳሳ፣ ሁንቴ እና በቆጂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎንደር፣ ባህርዳር፣ ወረኢሉ እና ሐሮ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ እና መልካጀብዱ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a strong cloud cover in the western, central, northeastern, eastern, and southern regions of our country. In connection with this, Mekelle, Adigrat, Shireendassalise, Adwa, Ayder, Maichew, Freweini, Lalibela, Wogeltiye, Kombolcha, Chefa, Mehalmeda, Mekaneslam, Gundomeskel, Alem Ketema, Enwari, De/Berhan, Fugendo, Abobo, Aira, Gimbi, Saltuka, Bedele, Arjo, Muk, Ijaji, Limugenet, Jimma, Wolisso, Bui, Adama, Nuraira, Abomsa, Balerobe, Jara, Ginr, Hirna, Chelenko, Harar, Addis Ababa, Aman, Tercha, Hosanna, Emdbir, Hawassa, Wolayta Sodo, Blate, Saula, Jinka, Arbaminch, West Abaya, Dilla, Burji, Chefe Donsa, Horodoyo, Akaki, Fencha, Ashi, Gubite, Bure, Feresbet, Rebue Gebeya, Shendi, Mekane Yesus, Atnago, Metu, Gololcha, Assasa, Hunte and Bekoji received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Gondar, Bahir Dar, Wereilu and Haro. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 35.0 degrees Celsius in Aisha, Dire Dawa, Metahara, and Melkajebdu.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ ቆራሄ፣ አፍዴር እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አቦቦ፣ አኮቦ፣ ዲማ፣ መንገሽ፣ ጋምቤላ ዙርያ፣ አንፊሎ፣ ጊዳሜ፣ ደምቢዶሎ፣ ጉሊሶ፣ ጃዊ፣ አምቦ ዙርያ፣ ጀልዱ፣ ግንደ በረት፣ አዳበርጋ፣ ኢሉገላን፣ ሻምቡ፣ ያያ ጉለሌ፣ ጫንጮ፣ ሱሉልታ፣ ፍቼ፣ ደጀን፣ ደብረኤልያስ፣ ሰዴ፣ ሁለትእጅ እነሴ፣ ሰከላ፣ ወረባቡ፣ ቃሉ እና ባቲ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ።
Tomorrow Weather conditions conducive to the formation of kiremet rains will continue to intensify in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, Bale; Addis Ababa; From Benishangul Gumuz Region, Asosa, Kamash, Mao Komo and Metekel zones; from Gambella Region, Majang, Nuer, Itang and Agnuak zones; from Southwestern Ethiopia Region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawro and West Omo zones; from Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, YEM liyu Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; all zones of Sidama Region; The Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region; the Jarar, Korahe, Afder and Fafen zones of the Somali region; and the Wolaita, Gamo, Gofa, Gedio, South Omo and Basketo zones of the Southern Ethiopia region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, numerical forecast indicates that Abobo, Akobo, Dima, Mengesh, Gambella area, Anfilo, Gidame, Dembidolo, Guliso, Jawi, Ambo area, Jeldu, Gend Beret, Adaberga, Ilugelan, Shambu, Yaya Gulele, Ancho, Sululta, Fiche, Dejen, Debre Elias, Sede, Binaye Enise, Sekela, Werebabu, Kalu and Bati will experience heavy rainfall that may cause flash floods within 24 hours.