Daily Weather Report 25 July 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ደባርቅ፣ አይከል፣ መተማ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ አዴት፣ ቻግኒ፣ ደንግላ፣ ላይበር፣ ደ/ወርቅ፣ ደ/ማርቆስ፣ ደ/ታቦር፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ አምባማርያም፣ ስሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ መካነሰላም፣ ጨፋ፣ እንዋሪ፣ መሀልሜዳ፣ ደ/ብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ፓዌ፣ ጉንዶመስቀል፣ ነጆ፣ ሻምቡ፣ አይራ፣ ደምቢዶሎ፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጂ፣ ካቺስ፣ ፍቼ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ ኑራኢራ፣ ኩሉምሳ፣ ባሌሮቤ፣ ጎሎልቻ፣ ጎሬ፣ በቆጅ፣ ዲንሾ፣ ቀርሳ፣ ሂርና፣ ግራዋ፣ ኩርፋጨሌ፣ መሰላ፣ መልካጀብዱ፣ ጨለንቆ፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ብላቴ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጅንካ፣ ተርጫ፣ ላሬ፣ አሽ፣ ሙጊ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነፋስ መውጫ፣ በሞጣ፣ በየትኖራ፣ በቡለን፣ ጊምቢ፣ ወሊሶ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ማሻ፣ ፉኝዶ፣ ጋምቤላ እና ኩሚ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ፣ ጭፍራ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was strong cloud coverage over the western half, central, northeastern, eastern, and southern parts of our country. In this regards, in Mekelle, Debark, Aykel, Metema, Gondar, Bahir Dar, Adet, Chagni, Dangla, Liber, Debre Work, Debre Markos, Debre Tabor, Lalibela, Wogltena, Amba Mariam, Sirinka, Combolcha, Mekansalam, Cheffa, Enewari, Mehalmeda, Debre Berhane, Sholagebeya, Pawe, Gundomeskel, Nedjo, Shambhu, Aira, Dembidolo, Arjo, Nekemte, Ejaji, Kachis, Fiche, Adama, Abomsa, Nuraera, Kulumsa, Bale Robe, Gololcha, Goro, Bekoji, Dinsho, Kerisa, Hirna, Girawa, Kurfachele, Mesala, Melekjbidu, Chelenko, Bui, Emdibir, Hosanna, Bilate, Wolayta Sodo, Jinka, Tercha, Lare, Ashi, Mugi and Addis Ababa, where light to moderate rainfall was recorded. Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm was noted in Nefasmewicha, Motta, Yetnora, Bullen, Gimbi, Woliso, Gore, Jimma, Masha, Fugnido, Gambella and Kumi. On the other hand, in Aisha, Dire Dawa, Metehara, Chifra, and Kebridehar, maximum temperatures of the day were recorded above 35.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በባቲ፣ ቃሉ፣ ስማዳ፣ ሁለትእጅነሴ፣ ሰዴ፣ ደጀን፣ ባሶሊበን፣ እንሳሮ፣ አንጎልላና ጠራ፣ ሞረትና ጅሩ፣ በረኸት፣ ደገም፣ ዋራጃርሶ፣ አባቦ፣ አባደንጎሮ፣ ሆሮ፣ ኪረሙ፣ ጊዳአያና፣ መርቲ፣ በአሴኮ፣ ፈንታሌ እና አርጎባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ መተሀራ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, the rain-giving weather events will intensify over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awusi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti zone; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Kamashi, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang, Itang, Nuwer and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. In addition, there will be heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours in Bati, Kalu, Simada, HuletEjnese, Sedae, Dejen, Basoliben, Ensaro, Angolelana Tera, Moretina Jiru, Berehet, Degem, Wara Jarso, Ababo, Abadengoro, Horo, Kiremu, Gidaayana, Merti, Aseko, Fentale and Argoba. On the other hand, the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Samara, Dubti, Mille, Elidar, Aisha, Chifra, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Cheffa, Metehara, and Kebridehar.