Daily Weather Report 25 July 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ ጎንደር፣ አምደወርቅ፣ ደብረታቦር፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ላይበር፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ መካነሰላም፣ ወገልጤና፣ አምባማሪያም፣ መሀልመዳ፣ ደብረብርሀን፣ ፓዌ፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ ደምቢዶሎ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ካቺሴ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ ሚኤሶ፣ ኩሉምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ባቱ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሐዋሳ፣ ቢላቴ፣ ጂንካ፣ ዲላ እና ሞያሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአዴት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጭፍራ፣ ጨፋ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 እስከ 45.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, over parts of the country that benefited from the Kiremt rain, had cloud coverage. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Debark, Gondar, Amdework, Debretabor, Shahura, Bahirdar, Dangila, Chagni, Laiber, Debrework, Debremarkos, Yetnora, Mekaneselam, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Pawe, Lare, Gambella, Dembidolo, Nekemte, Shambu, Kachise, Weliso, Bishoftu, Adama, Mieso, Kulumsa, Arsirobe, Balerobe, Batu, Emdibir, Hosanna, Werabe, Hawassa, Bilate, Jinka, Dilla, and Moyale. Heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Adet. On the other hand, in Chifra, Cheffa, Elidar, Gewane, and Awash Arba, the maximum daily temperature was recorded between 35.0 and 45.8 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ ማኦኮሞ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጭፍራ፣ ቆሪ፣ ዱብቲ፣ ኤሊዳር፣ ቋራ፣ ባቲ፣ ደዋጨፋ፣ ወረባቦ፣ አምባሰል፣ ምንጃርሸንኮራ፣ በረሐት፣ አንጎለላና፣ ሞረትናጅሩ፣ መራቤቴ፣ አኮቦ፣ ጆሬ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ፣ መንገሽ፣ ጎደሬ፣ ጉባ፣ ዳንጉረ፣ ሸርኮሌ፣ ማኦኮሞ፣ ጉራፈርዳ፣ ሸኮ፣ ቤንች፣ ቸሃ፣ የኪ፣ ደቻ፣ ጊዳሚ፣ አንፊሎ፣ ደዴሳ፣ ኖኖ፣ ጅባት፣ አመያ፣ አዳአባርጋ፣ ሜታሮቢ፣ ገርበጉራቻ፣ ደገም፣ ጊምቢቹ፣ አዳአ እና ቦሴቲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ እጅግ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ሚሌ፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሀራ እና መልካጀበዱ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
For the upcoming day, areas of the country benefiting from the Kiremt rain will have strong and widespread cloud coverage and accumulation. In this respect, the west, central, north west, south east, south and east zones of Tigray region; the west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo national special zone, north Shewa and Waghemra zones of Amhara region; Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones of Afar region; Metekal, Kamashi, Mao Komo and Asossa zones of Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones of Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Majang, Nuwer, Itang and Agnuak zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones of the south west Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones of the central Ethiopia region; Walaita, Basketo, Gofa, Gamo, Burji, Kore, Gardula, south Omo and Gedeo zones of the south Ethiopian region and the Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. Moreover, Chifra, Kori, Dubti, Elidar, Quara, Bati, Dewachefa, Werebabo, Ambasel, Minjarshenkora, Berehat, Angolela, Moretinajru, Merabete, Akobo, Jore, Abobo, Gambella, Mengesh, Godere, Guba, Dangur, Sherkole, Mao Komo, Guraferda, Sheko, Bench, Cheha, Yeki, Decha, Gidami, Anfilo, Dedesa, Nono, Jibat, Ameya, Adabarga, Metarobi, Gerbegurecha, Degam, Gimbichu, Ada’a and Boseti will experience extremely heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum daily temperature in Samara, Mile, Aisha, Awash Arba, Metehara, and Melkajebedu will be recorded above 38 degrees Celsius.