Daily Weather Report 25 July 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ደ/ ታቦር፣ ፓዌ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ነፋስ መውጫ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ አ/ ማርያም፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ የትኖራ፣ ደ/ ማርቆስ፣ ላይበር፣ እንዋሪ፣ ሾላገበያ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ ካቺስ፣ ፍቼ፣ ወሊሶ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ኑራኢራ፣ ኩሉምሳ፣ ባቱ፣ ቢኢ፣ አቦምሳ፣ ቁልቢ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ሰኮሩ፣ ወራቤ፣ ቦሬ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጅንካ እና አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በተርጫ እና ደ/ ብርሃን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ፣ ጨፋ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the northwest, central, west and eastern parts of our country. In this regards, in Debark, Aykel, Shahura, Bahir Dar, Debr Tabor, Pawe, Chagni, Dangla, Adet, Motta, Nefasmewicha, Wegeltena, Combolcha, Amba Maryam, Cheffa, Mekansalam, Yetnora, Debr Markos, Leiber, Enwari, Sholagebeya, Asossa, Nedjo, Gimbi, Gore, Chira, Gidayana, Shambhu, Ejaji, Kachis, Fiche, Woliso, Limugenet, Jimma, Adama, Nuraera, Kulumsa, Batu, Bui, Abomasa, Kulubi, Dire Dawa, Jigjig, Emdibir, Hosanna, Sokoru, Werabe, Bore, Tepi, Aman, Wolayta Sodo, Jinka, and Addis Ababa received light to moderate amounts of rainfall and Heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Tercha and Debre Birhan. On the other hand, maximum temperature of the day was exceeded 35.0 degrees celsius in Aisha, Dire Dawa, Metehara, Cheffa, and Kebridehar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። በተጨማሪም በአሄፈሮም፣ ጓንጓ፣ ፓዌ፣ አርጆ፣ ኖኖ ኩመባ፣ ጉቶጊዳ፣ ዲጋ፣ ኖኖ፣ አምቦ ዙሪያ፣ ደንዲ፣ አመያ፣ ወንጭ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙሴቃ፣ ቸሃ፣ ጊቤ፣ እና አቃቂ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, the rain-giving weather events will intensify over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Borena, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti zone; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang, Nuwer and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall, which will significantly benefit agricultural activities and water availability. In addition, in Aheferom, Guangua, Pawe, Arjo, Nonno Kumeba, Gutogida, Diga, Nono, Ambo Zuriya, Dendi, Amaya, Wenchi, Sokoru, Limuseka, Cheha, Gibe, and Akaki are expected to have heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours. On the other hand, in Semera, Dubti, Mille, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Dire Dawa, Metehara, and Kebridehar, the daily maximum temperature will exceed 38 degrees Celsius.