Daily Weather Report 25 July 02

Weather Summary for previous day

July 1, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአድዋ፣ መቀሌ፣ ማይጨው፣ ደባርቅ፣ ሸሁራ፣ ባህርዳር፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ መካነሰላም፣ መሃልሜዳ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ አምባማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ስሪንቃ፣ ጉንዶመስቀል፣ አዲስ አበባ፣ ወሊሶ፣ ካችስ፣ ሻምቡ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጂ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ በደሌ፣ ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ፣ ገለምሶ፣ ቦሬ፣ ሆሚ፣ ነገሌ፣ ሆሳዕና፣ ተርጫ፣ ማጅ፣ ማሻ እና በቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በየትኖራ፣ በአይከል፣ በጋምቤላ እና በፉኝዶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ ሸዋሮቢት፣ መተሀራ፣ መልካጀብዱ እና ቀብሪደሀር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.0 እስከ 45.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover over the Kiremt rain benefiting areas of the country. In line with this, in Adwa, Mekelle, Maichew, Debark, Shahura, Bahir Dar, Adet, Motta, Debre Markos, Mekansalam, Mehalmeda, Lalibela, Wegeltena, Amba Mariam, Combolcha, Cheffa, Sirinka, Gundomeskel, Addis Ababa, Woliso, Kachis, Shambhu, Aira, Nekemte, Ejaji, Chira, Jimma, Sokoru, Bedele, Gimbi, Dembidolo, Gemelso, Bore, Homi, Negele, Hosanna, Tercha, Maji, Masha and Tepi received light to medium amounts (1-29 mm) of rainfall). Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Yetnora, Aykel, Gambella, and Fugnido within 24 hours. On the other hand, in Semara, Aisha, Chifra, Awash Arba, Dire Dawa, ShewaRobit, Metehara, Melekjbidu, and Kebridehar the maximum temperature of the day was recorded ranging from 37.0 to 45.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

July 3, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዋጅራት፣ ሳምረ፣ ህንታሎ፣ ጨርጨር፣ ኦፍላ፣ ራያ አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ ደሃና፣ በየዳ፣ ላስታ፣ ቡግና፣ ጉባላፍቶ፣ ጊዳን፣ አምባሰል፣ ወረባቦ፣ ኩታበር፣ ደሴ ዙሪያ፣ ባቲ፣ ዳዋጨፋ፣ ላይጋንት፣ ስማዳ፣ ግሽሮቢ፣ ኤፍራታናግድም፣ ቀወት፣ ያንጉዲ፣ ዳሊፋጌ፣ ከለአሉ፣ ጊምቢቹ፣ አዳአ፣ አቃቂ፣ ሙኒሳ፣ አመያ፣ ሶኮሩ፣ ቦቶርጦላይ፣ አበሸጌ፣ ቸሃ፣ ጉቶጊዳ፣ ሳሲጋ እና ሊሙ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ እና መተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be widespread and intensified cloud cover with accumulation over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awusi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti and Fafen zones; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Kamashi, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang, Itang and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, south Omo and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. Additionally, due to the occasional intensifying weather events, there will be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours in Wajrat, Samre, Hintalo, Chercher, Ofla, Raya Alamata, Sekota, Dehana, Beda, Lasta, Bugna, Gubalafto, Gidan, Ambassal, Werebabo, Kutaber, Dessie Surround, Bati, Dawa Cheffa, Laygaynt, Simada, Gishrobi, Ephratanagdim, Kewot, Yangudi, Dalifage, Kelealu, Gimbichu, Adaa, Akaki, Munisa, Amaya, Sokoru, Botortolai, Abeshige, Cheha, Gutogida, Sasiga, and Limu. On the other hand, in Samara, Dubti, Mille, Elidar, Aisha, Gewane, Dalifagi, Awash Arba, Dire Dawa, and Metehara the maximum temperature of the day will be expected 38 degrees Celsius.