Daily Weather Report 25 July 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ መተማ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመውጫ፣ ላሊበላ፣ ደበረወርቅ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መካነሰላም፣ የትኖራ፣ መሃልሜዳ፣ እንዋሪ፣ ሾላገበያ፣ ጉንዶመስቀል፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጂ፣ ወሊሶ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ደምቢዶሎ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ ኩልምሳ፣ አቃቂ፣ ሆሚ፣ ሆርዶየ፣ ፊንጫ፣ ጨፌዶንሳ፣ ቁሉቢ፣ ግራዋ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ማንኩሽ፣ ፓዌ፣ ቡለን፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ጂንካ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ዲላ፣ ቢላቴ፣ ጋምቤላ እና ሙጊ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡኢ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአይሻ፣ መተሀራ፣ ጨፋ፣ ቀብሪደሀር፣ ድሬዳዋ እና መልካ ጀብዱ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.0 እስከ 41.0 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the western half, central, northeast, east, and southern parts of the country. In line with this, Metema, Aykel, Shahura, Debark, Gondar, Bahir Dar, Debretabor, Windsor, Lalibela, Debrework, Dangla, Chagni, Mekansalam, Yetnora, Mehalmeda, Enwari, Sholagebeya, Gundomeskel, Shambu, Nekemte, Ejaji, Woliso, Gimbi, Aira, Gore, Jimma, Dembidolo, Addis Ababa, Adama, Abomasa, Kulumsa, Akaki, Homi, Horodoye, Fincha, Chefedonsa, Kulubi, Girawa, Bore, Negele, Mankush, Pawe, Bullen, Masha, Tercha, Jinka, Wolaitasodo, Sawla, Dilla, Bilate, Gambella, and Mugi. They experienced light to medium rainfall, receiving between 1 to 29 mm, with heavy rainfall exceeding 30 mm recorded in Bui. Conversely, Aisha, Metehara, Chefa, Kebridehar, Dire Dawa, and Melka Adventure reported maximum daily temperatures ranging from 37.0 to 41.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጉሎመቀዳ፣ ጋንታአፍሹም፣ ዋጅራት፣ ራያ አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ ደሃና፣ በየዳ፣ ጠለምት፣ ላስታ፣ ቡግና፣ ጉባላፍቶ፣ ጊዳን፣ ላይጋንት፣ ደገም፣ ግራርጃርሶ፣ ቅምብቢት፣ አዳበርጋ፣ ሜታሮቢ እና በኖኖ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር፣ አይሻ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ እና መተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow,, the rain-giving weather events will intensify over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In association with this, from Tigray region central, northwest, southeast, south, and east zones; from Amhara region north, south, and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, the Oromo ethnic special zone, north Shewa, and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Kelem, and Horogudru Wellega, west, southwest, east, north, and west Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji, and west Guji zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Afar region Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones; from Somali region Siti zone; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Mao Como, and Metekel zones; from Gambella region Majang and Angwuak zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, and west Omo zones; from Central Ethiopia region's Gurage, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadia, Kembata, and Tembaro zones; all zones of the Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones will receive light to moderate amount of rainfall. Additionally, there will be heavy rainfall of more than 30 mm within a 24-hour in Gulomaqada, Gantafishum, Wajrat, Raya Alamat, Sekota, Dehana, Beyeda, Tselemt, Lasta, Bugna, Gubalafto, Gidan, Lay Gaynt, Degem, Girar Jarso, Kimbibit, Adaberga, Meta Robi and Nono. Therefore, the rainfall amount and distribution will be very essential for carrying out agricultural activities.