Daily Weather Report 25 Jan 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሻምቡ፣ በካቺስ፣ በአንገርጉትን፣ በአርጆ፣ በጭራ፣ በማሻ፣ በቴፒ እና በማጂ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል:: ይሁን እንጂ በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, there were clouds in the southwest, south and central parts of the country. In this regard, light rains were recorded in Shambu, Kachis, Angergut, Quara, Masha, Tepi and Maji. However, dry, sunny and windy bega weather has been observed in the northeastern and eastern parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና በከፋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow there will be cloud cover over the southwest, south, central and northeast areas of our country. In relation to this, numerical forecast data indicates that Jimma, Ilubabor, Buno Dele, Sheka, Bench Sheko and Keba zones will receive light amount of rain in a few places. On the other hand, the northern and eastern parts of the country experience sunny and windy bega weather.