Daily Weather Report 25 Jan 30

Weather Summary for previous day

Jan. 29, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወላይታ ሶዶ፣ በቦሬ እና በአዲስ አበባ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል:: ይሁን እንጂ በሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the southwest, south, central, and northeast parts of the country. In this regard, light rain was recorded in Walaita Sodo, Bore, and Addis Ababa. However, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in the northwest and east parts of the country.

Weather Forecast for next day

Jan. 31, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Tomorrow, the southwest, south, central, and northeast parts of our country will have cloud coverage. In line with this, Jimma, Ilubabor, west Arsi, west Guji, Walaita, Gamo, Gofa, south Omo, Gedeo zones, and Sidama region zones will experience light rain at a few places. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather will be observed over the northern, northwestern, and eastern areas of the country.