Daily Weather Report 25 Jan 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፍቼ፣ ጊምቢ፣ ኢጃጂ፣ ወሊሶ፣ ሊሙ ገነት፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ቡሌሆራ፣ ሳውላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ብላቴ እና ዲላ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, they had cloud cover over the southwest, south and central parts of the country. Meanwhile, light rainfall was recorded in Fiche, Gimbi, Ejaji, Woliso, Limu Gent, Jimma, Chira, Bulehora, Saula, Wolaita Sodo, Bilate and Dila. On the other hand, dry, sunny and windy bega weather has been observed in the north-west and east parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፤ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow there will be cloud cover over the southwest, south, central and northeast areas of our country. Along with this, Jimma, Ilubabor and West Shewa zones from the Oromia region; Sheka, Bench Sheko, Dauro and Konta zones from South West Ethiopia region; From the Central Ethiopia Region, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kambata and Tmbaro Zones; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro; Derashe, South Omo and Gedo zones; You will get light rain from West and East Gojam zones of Amhara region and Kalbeti zone from Afar region. On the other hand, the north-western and eastern parts of the country have dry, sunny and windy Bega.