Daily Weather Report 25 Jan 28

Weather Summary for previous day

Jan. 27, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዳንግላ 3.0፣ በአዲግራት 5.0፣ በወገልጤና 5.0፣ በሾላገበያ 4.2 እና በጅግጅጋ 4.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in the northwest, northeast, and east parts of the country. Along with this, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Dangila 3.0, Adigrat 5.0, Wegeltena 5.0, Sholagebeya 4.2 and Jigjiga 4.2. Conversely, there was cloud coverage over the southwestern, southern, and central areas of the country.

Weather Forecast for next day

Jan. 29, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፤ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል በጥቂት ምስራቅ ዞን፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡

For the upcoming day, cloud coverage will be over our country's southwestern, southern, central, and northeastern parts. According to this, from Oromia region Jimma, west Arsi, Guji, and west Guji zones; from southwest Ethiopia region Dawuro and Konta zones; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata, and Tembaro zones; from south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro; Derashe, south Omo and Gedeo zones; Sidama region zones, few place of eastern zone of Tigray region; from Amhara region north and south Wollo zones and Afar region Kilbeti zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In contrast, the northwestern and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather.