Daily Weather Report 25 Jan 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዳንግላ 4.5፣ በወገልጤና 5.0፣ በመሀልሜዳ 4.0፣ በሾላገበያ 4.1፣ በቡኢ 4.6 በሐሮማያ 4.8 እና በጅግጅጋ 4.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና በጭራ፣ ሶኮሩ፣ በቴፕ እና በማጂ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል::
Yesterday, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in the north West, central, north east, and east parts of the country. As a result, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Dangila 4.5, Wegeltena 5.0, Mehalmeda 4.0, Sholagebeya 4.1, Bui 4.6, Haromaya 4.8 and Jigjiga 4.0. On the other hand, the southwest and southern parts of the country had cloud coverage, with light rain recorded in Chira, Sokoru, Tepi, and Maji.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳዉሮ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፤ ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow, the southwest, south, northeast, and central parts of our country will have better cloud coverage. Consequently, from Oromia region Jimma, southwest Shewa, west Arsi, Borena, Guji and west Guji zones; from the southwest Ethiopia region Dawuro zone; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Burji, Amaro and Gedeo zones and Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. However, the Bega dry, sunny, and windy weather will be observed in the north, northwest, and east areas of the country.