Daily Weather Report 25 Jan 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጤና 3.8፣ በዳንግላ፣ 4.0፣ በባቲ 5.0፣ በደብረብርሀን 3.6፣ በሾላገበያ 3.0፣ በቢሾፍቱ 3.2፣ በቡኢ 3.4፣ በእምድብር 3.5፣ በሐሮማያ 2.0፣ በአርሲሮቤ 3.5 እና በጅግጅጋ 0.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in most parts of the country. Accordingly, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Wegeltena 3.8, Dangila 4.0, Bati 5.0, Debrebrehan 3.6, Sholagebeya 3.0, Bishoftu 3.2, Bui 3.4, Emdibir 3.5, Haromaya 2.0, Arsirobe 3.5 and Jigjiga 0.6.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በደብረብርሀን፣ በሾላገበያ፣ በቡኢ፣ በእምድብር፣ በቢሾፍቱ፣ በአርሲሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the northwest, northeast, central, and eastern portions of our country will have the Bega dry, sunny, and windy weather. Consequently, the numerical weather forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Maichew, Debark, Dangila, Wegeltena, Bati, Debrebrehan, Sholagebeya, Bui, Emdibir, Bishoftu, Arsirobe, Haromaya and Jigjiga. Conversely, there will be cloud coverage in the south west and south areas of the country, with light rainfall expected in a few places.