Daily Weather Report 25 Jan 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ከፍተኛ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ንፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዳንግላ፣ በደብረ ብርሀን፣ በወገል ጤና፣ በባቲ፣ በሐሮማያ፣ በቢሾፍቱ፣ በእምድብር፣ በቡኢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50c በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በማሻ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northeast, east, central, northwest and southern highlands of the country experienced by the bega’s dry, sunny and windy weather conditions. In addition, the daily minimum temperature was recorded below 50c in Dangila, Debre Berhan, Wegel Tena, Bati, Haromaya, Bishoftu, Emdbir, Bui and Jigjiga. On the other hand, the southern and southwestern parts of the country had cloud coverage and light rain was recorded in Masha.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በአዴት፣ በወገል ጤና፣ በባቲ፣ በደብረ ብርሀን፣ በጅማ፣ በቡኢ፣ በዳንግላ፣ በሾላ ገበያ፣ በሐሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በቢሾፍቱ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50c በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በሌላ በኩል ደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል አርሲና ጉጂ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For tomorrow, the north, northwest, west, central and eastern parts of the country will be expected by bega’s dry, sunny and windy weather conditions. Therefore, numerical forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 50c in Adet, Wegel Tena, Bati, Debre Berhan, Jimma, Bui, Dangila, Shola Gebeya, Haromaya, Arsi Robe, Bishoftu and Jigjiga. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and southwest parts of the country. In line with this, light rain will be expected in the Arsi and Guji zones of the Oromia region.