Daily Weather Report 25 Jan 22

Weather Summary for previous day

Jan. 21, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ በመሆኑም በዳንግላ አዴት፣ በወገልጤና ፣ አ/ማርያም፣ በባቲ፣ በይትኖራ፣ በደ/ብርሃን፣ በሾላ ገበያ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእምድብር፣ በጅማ፣ በኩሉምሳ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 50 C በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday Dry, sunny and windy weather was observed in the northwest, northeast, central and eastern parts of our country. Therefore, the minimum temperature of the day was recorded below 50 C in Dangla, Adet, Wegaletena, A/Maryam, Bati, Yetnora, De/Beharn, Shola Gebeya, Bishoftu, Bui, Emdiber, Jimma, Kulumsa, Arsi Robe, Haromaya and Jigjiga.

Weather Forecast for next day

Jan. 23, 2025

በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በወገልጤና፣ በአለምከተማ፣ በደ/ብርሃን፣ በሾላ ገበያ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 50 C በታች እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, most parts of our country will experience the dry, sunny and windy weather of Bega. Along with this, our digital forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 50 C in Debark, Dangla, Wegletena, Alem Ketema, De/Berahn, Shola Gebeya, Bishoftu, Bui, Haromaya and Jigjiga.